ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ወጣቶች በኩባንያዎች ያላቸው ተፈላጊነት ለምን ቀነሰ?
በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ ጥናት ኩባንያዎች ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ሰዎችን ስራ ለመቅጠር ያላቸው ፍላጎት ቀንሷል ተብሏል
ቀጣሪዎች ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ሰዎች የስራ ተነሳሽነት እና ችግርን የመፍታት ብቃት ይጎድላቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል
ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ወጣቶች ለምን በኩባንያዎች ያላቸው ተፈላጊነት ቀነሰ?
ከ1990 ዓ.ም ወዲህ የተወለዱ ሰዎች በተለምዶ የዜድ ትውልድ ወይም ጄን ዜድ በመባል ይጠራሉ፡፡
በቅርቡ ኢንተሊጀንት የተሰኘ ዓለም አቀፍ የትምህርት እና ስራ አማካሪ ተቋም ባወጣው ሪፖርት ይህ ትውልድ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የስራ ክህሎቶች ይጎድለዋል ተብሏል፡፡
ዩሮ ኒውስ ይህን ጥናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ጥናቱ 1 ሺህ ስራ ቀጣሪ ስራ አስኪያጆችን ያሳተፈ ሲሆን ከስድስቱ አመራሮች አንዱ የዜድ ትውልድ ምሩቃንን ስራ ለመቅጠር ፍላጎት የላቸውም፡፡
ቀጣሪዎቹ ይህን ትውልድ በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ፣ ችግሮችን የማይቋቋም፣ የተግባቦት ችግር ያለባቸው ናቸው ሲሉ ይገልጿቸዋል፡፡
በተለይም ከ1990 እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜ የተወለዱ ወጣቶች አስተያየቶችን ያለመቀበል፣ የስራ ስነ ምግብር የሌላቸው እና ለጥረት ብዙም ፍላጎት የሌላቸው ናቸውም ተብሏል፡፡
በካሊፎርኒያ ዩንቨርሲቲ የቢዝነስ መምህር የሆኑት ሆሊ ሽሮዝ እንዳሉት ዜድ ትውልድ ከስራ መሪዎቻቸው ጋር ጥሩ መግባባትን መፍጠር ላይ ትልቅ ድክመት እንዳለባቸው፣ ስራቸውን ለማሻሻል ተጨማሪ ስልጠናዎችን የመውሰድ ፍላጎት የሚጎድላቸው ናቸውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሚሊኒየሙ ትውልድ ከቀድሞው ትውልድ የበለጠ ለካንሰር ተጋላጭ መሆኑን ጥናት አመለከተ
ይህ ትውልድ በተለይም ከደንበኞች ፣ ስራ ባልደረቦቻቸው እና ተገልጋዮች ጋር ጥሩ ግንኙነትን መፍጠር ያለመቻል ችግርም እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የዚህ ተውልድ አባላት ከምረቃቸው በኋላ ስራ የመስራት ፍላጎት ከማጣት ባለፈ ማመልከቻዎችን አለመሙላት፣ በቤተሰቦቻቸው ላይ ጥገኛ መሆን እና ለስራ ቃለ መጠይቅ ሲጠሩ ወላጆቻቸውን ይዘው መሄድ ፍላጎት እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ቀጣሪ ኩባንያዎች እና ስራ አስኪያጆች ዜድ ትውልድን ችግር አለባቸው በሚል ከስራ ከማሰናበት ይልቅ ችግሮች እንዳለባቸው አምነው ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ምክረ ሀሳብ ቀርቦላቸዋል፡፡