የሰው ኃይል ልማት ለሀገራት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?
የጤና አገልግሎቱ የተሻለ በሆነበት ሀገር ያለ ህዝብ ለበሽታ ያለው ተጋላጭነት ይቀንሳል፣ የእድሜ ጣሪያው ከፍ ይላል
በትምህርት እና በጤና ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ጤናማ እና ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲኖር ያደርጋል
የሰው ኃይል ልማት ለሀገራት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?
የሰው ኃይል ልማት በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ነገሮች ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
አስፈላጊ የሚሆንባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
1)የኢኮኖሚ እድገት
በትምህርት እና በጤና ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ጤናማ እና ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲኖር ያደርጋል። ይህም ምርታማነት እንዲጨምር ፣ ፈጠራ እንዲኖር እና የኢኮኖሚ እድገትን እንዲመዘገብ ያስችላል።
2) ማህበራዊ መረጋጋት
የተሻለ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ተደራሽነት እና ጤና ድህነትን በመቀነስ ማህበራዊ መስተጋብር እና የተረጋጋ ሀገር እንዲኖር ያስችላል
3) አለምአቀፋዊ ውድድር
ብቃት ያለው፣ መፍጠር የሚችል እና ተለዋዋጭነትን መልመድ የሚችል የሰው ኃይል ያላቸው ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ናቸው።
4) ጤናማ ህዝብ
የጤና አገልግሎቱ የተሻለ በሆነበት ሀገር ያለ ህዝብ ለበሽታ ያለው ተጋላጭነት ይቀንሳል፣ የእድሜ ጣሪያው ከፍ ይላል
5) ዝቅተኛ የድህነት መጠን
የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ሁልጊዜ ድህነት የመቀነስ አላማ አላቸው። የተሻሻለ የኑሮ ሁኔታን በመፍጠር ከድህነት አዙሪት ለመውጣት የሰው ኃይል ልማት ወሳኝ መሆኑ እሙን ነው።
6) የአካባቢ ዘላቂነት
የተማረ ህዝብ ስለአካባቢያዊ ጉዳዮች የነቃ ስለሚሆን ለረጅም ጊዜ የስነምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ የሚረዳ ዘላቂነት ያለው ልማትን ይሰራል