የምርጥ አደራዳሪ የሚባለው ምን ሲያሟላ ነው?
ድርድር ለማመቻቸት የሚያስችል ጠንካራ የንግግር ችሎታ ያስፈልጋል
ድርድሮችን በውጤት ለማጠናቀቅ አንድ አደራዳሪ ሊያሟላቸው የሚገቡ ባህርያት እና አቅምች ይኖራሉ
የምርጥ አደራዳሪ የሚባለው ምን ሲያሟላ ነው?
ድርድሮችን በውጤት ለማጠናቀቅ አንድ አደራዳሪ ሊያሟላቸው የሚገቡ ባህርያት እና አቅምች ይኖራሉ። እዚህ የተጠቀሱት ዋናዋናዎቹ ናቸው።
1) ገለልተኝነት፦ በድርድሩ ከሚካፈሉ አካላት ገለልተኛ መሆን ወይም አድሎ አለመፈጸም
2) የተግባቦት ችሎታ
ድርድር ለማመቻቸት የሚያስችል ጠንካራ የንግግር ችሎታ
3)ስሜትን መረዳት
የሁሉንም አካላት ስሜት እና አተያይ መረዳት እና እውቅና መስጠት
4) ችግር የመፍታት ችሎታ
በድርድሩ ወቅት ቀልፍ ሀሳቦችን መለየት እና መፍትሄዎችን መፈለግ
5)ትግስት
ጊዜ በሚወስድ እና ጠንካራ ክርክር በሚኖርበት ጊዜ ትግስት ማድረግ
6) ተለዋዋጭነት
ተለዋዋጭ በመሆን ለተለያዩ ሰዎች እና ሁኔታዎች የሚመቹ ስትራቴጂዎችን መንደፍ
7)ሚስጥር ጠባቂነት
በድርድሩ ሂደት ሚስጥር መጠበቅ እና ሙያዊ ስነምግባር በመላበስ መንቀሳቀስ
8) ስነምግባር
የስነምግባር መርሆዎችን በመከተል መንቀሳቀስ እና ድርድሩን በሀቀኝነት መምራት
9) ለባህል ጥንቃቄ መስጠት
ድርድሩን ሊጎዱ የሚችሉ የባህል ልዩነቶችን ማክበር እና መረዳት
10) አለመሰልቸት
አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮች የሚያጋጥሙበት ጊዜ ቢፈጠርም፣ ያለመሰልቸት መፍትሄ ለማምጣት ፍቃደኛ መሆን