የህዝብ ቆጠራ ማካሄድ ለምን ይጠቅማል?
የህዝብ ቁጥር መታወቁ ሀገራት እና ድርጅቶች መሉ እውቀት እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል
ሀገራት በየተወሰነ አመታት ልዩነት የህዝብ ቆጠራ ወይም "ፖፑሌሽን ሴንሰስ" ያካሄዳሉ
የህዝብ ቆጠራ ማካሄድ ለምን ይጠቅማል?
ሀገራት በየተወሰነ አመታት ልዩነት የህዝብ ቆጠራ ወይም "ፖፑሌሽን ሴንሰስ" ያካሄዳሉ።
ጥቅሙ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
የህዝብ ቁጥር መታወቁ ሀገራት እና ድርጅቶች መሉ እውቀት እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል።
ዝርዝር የሆነ ዲሞግራፊ ወይም የህዝብ አሰፋፈር ሁኔታን የሚያሳይ መረጃ፣ ሀብትን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማከፋፈል፣ መሰረተልማት ለመገንባት እና የህዝብ ፍላጎትን ያለማከለ ፖሊሲ ለማዘጋጀት ወሳኝ ነው።
ሴንሰስ በጊዜ ሂደት የሚፈጠሩ አዳዲስ ሁነቶችን፣ የፍልሰት ሁኔታን እንዲሁም የእድሜ እና የጎሳ ስርጭት ልዩነቶችን ለማወቅ ያስችላል።
የሴንሰስ መረጃ የምርጫ ክልሎች በመክፈል ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። ይህ የእያንዳንዱን ሰው ድምጽ እኩል ዋጋ እንዳው ዋስትና ይሰጣል።
በአጠቃላይ ፖፑሌሽን ሴንስ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመወሰን መሰረታዊ ነው።