ሩሲያ ባስወነጨፈችው ሚሳይል የዩክሬንን ወታደራዊ መሰረተልማት መምታቷን ገለጸች
ዩክሬን ተጠቅቷል ስለተባለው ወታደራዊ መሰረተልማት ጉዳይ ያለችው ነገር የለም
ሩሲያ ጥቃቱን መቼ እንደፈጸመችው ባትገልጽም ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገጹ በፖሰተው ቪዲዮ ከመርከቧ ላይ ሚሳይል ሲተኮስ ያሳያል
ሩሲያ ባስወነጨፈችው ሚሳይል የዩክሬንን ወታደራዊ መሰረተልማት መምታቷን ገለጸች።
ሩሲያ ከጥቁር ባህር ላይ ባስወነጨፈችው ክሩዝ ሚሳይል የዩክሬንን ወቲደራዊ መሰረተ ልማት መምታቷን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬ እለት አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገጹ እንደገለጸው "የፍሪጌት ጥቁር ባህር ፍሊት አባላት የጠላትን ወታደራዊ መሰረተልማት እንዲመቱ ትዕዛዝ ውስደዋል"።
የተፈለገው ኢላማ ተመቷል ብሏል ሚኒስቴሩ።
ሮይተስ ጉዳዩን በገለልተኝነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል። ዩክሬን ተጠቅቷል ስለተባለው ወታደራዊ መሰረተልማት ጉዳይ ያለችው ነገር የለም።
ሩሲያ ጥቃቱን መቼ እንደፈጸመችው ባትገልጽም ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገጹ በፖሰተው ቪዲዮ ከመርከቧ ላይ ሚሳይል ሲተኮስ ያሳያል።
የዩክሬን ባህር ኃይል በትናንትናው እለት የሩሲያ ባህር ኃይል ካሊበር ሚሳይል የታጠቁ ሁለት ባህር ሰርጓጅ መርከቦችን በጥቁር ባህር በተጠንቀቅ ማቆሙን ገልጾ ነበር።
ዩክሬን በጥቁር ባህር በሚገኙ የሩሲያ ወታደራዊ ተቀማት ላይ የድሮን ጥቃት በማድረስ በርካታ ውድመቶችን አድርሳለች።
ሩሲያ በጥቁር ባህር ያለውን የጦር ኃይሏን በዩክሬን ላይ የረጅም ርቀት ሚሳይል እንዲያስወነጭፉ እያደረገች ነው።
21 ወራትን ያስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሁንም ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል።