የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ስለሚሰነዘረው ጥቃት ለምን ሳይስማማ ቀረ?
የእስራኤል ካቢኔ በዛሬው ዕለት ያደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቋል ተብሏል
እስራኤል የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ለደረሰው የድሮን ጥቃት የኢራን እጅ አለበት ማለቷ ይታወሳል
የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ስለሚሰነዘረው ጥቃት ለምን ሳይስማማ ቀረ?
ከአንድ ዓመት በፊት በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት መቋጫ ያላገኘ ሲሆን በየዕለቱ አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
በጦር ካቢኔ እየተመራች ለችው እስራኤል በዛሬው ዕለት በኢራን ላይ ሊወሰድ በታሰበው እርምጃ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጋለች፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ ከሰሞኑ በቄሳሪያ በሚገኘው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ከሂዝቦላህ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሮበታል፡፡
ከዚህ የሂዝቦላህ ጥቃት ጀርባ ኢራን እጇ አለበት መባባን ተከትሎ በቴህራን ላይ ሊወሰድ ስለታሰበው ጥቃት የዛሬው የሀገሪቱ ካቢኔ መወያያ አጀንዳ እንደነበር የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
እንደዘገባዎቹ ከሆነ የእስራኤል ጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ሊወሰዱ ሰለታሰቡት እርምጃዎች ላይ ያለ ስምምነት የተጠናቀቀው አሜሪካ በአንድ ወር ውስጥ በጋዛ ላሉ ዜጎች ያለው የሰብዓዊ መብት ካልተሻሻለ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አቋርጣለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቷ፣ እስራኤል ከተመድ ጋር ያላት ግንኙነት አለመሻሻሉ እና የሐማስ አዛዥ ያህያ ሲንዋር መገደል የታገቱ እስራኤላዊን ሊለቀቁ ይችላሉ የሚል ተስፋ መምጣቱ በኢራን ላይ ሊወሰድ በታሰበው ጉዳይ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል፡፡
የእስራኤል ከፍተኛ ወታራዊ አዛዥ በሰሜን ጋዛ ውስጥ ተገደለ
ከዚህ በተጨማሪም የመጨረሻ እርምጃ ውሳኔዎች የሚወሰኑት በድንገት መሆኑ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋል መባሉ እና የእስራኤል እና ተመድ ግንኙነት በዚሁ ከቀጠለ እስራኤል ከተመድ የመባረር እጣ ሊገጥማትም ይችላል የሚለው ስጋት ለውሳኔው መዘግየት መባሉ ሌላኛው ስጋት ነው ተብሏል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የእስራኤል ከፍተኛ አዋጊ በሰሜናዊ ጋዛ መገደሉን ተከትሎ በጋዛ እና ሊባኖስ ከባድ ድብደባዎችን በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡