ኒኩሌር ታጠቂ የሩሲያ የጦር መርከቦች የአሜሪካ ጎረቤት ወደሆነችው ኩባ ለምን ተጓዙ?
አራት የሩሲያ የጦር መርከቦች ከአሜሪካ 145 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መልህቃቸውን ጥለዋል
አሜሪካ የመርከቦች ኩባ መድረስ ስጋት አይፈጥርብኝም ብትልም፤ በቅርበት እየተከታተለች ነው
ሩሲያ በኑክሌር ኃይል የሚንቀሳቀስ የባሕር ሰርጓጅን ጨምሮ አራት መርከቦቿን የአሜሪካ ጎረቤት ወደሆነችው ኩባ መላኳ በቀጠናው አስዲስ ውጥረትን ፈጥሯል።
አራት የሩሲያ ግዙፍ የጦር መርከቦች ከአሜሪካ ፍሎሪዳ በ145 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመትገኘው ሃቫና ቤይ የባህር ዳርቻ ላይ ባሳለፍነው ረቡዕ መልህቃቸውን ጥለዋል።
የሩሲያ የጦር መርከቦች ወደ ኩባ ሲጓዙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባይሆንም አሁን ላይ ወደ ሃቫና ያቀናው የሩሲያ የባህር ኃይል መርከብ እስካሁን ከነበሩት ግዙፉ ነው ተብሏል።
ባሳለፍነው ረቡዕ ኩባ ሃቫና የደረሱት የሩሲያ የጦር መርከቦች እስከ ፊታችን ሰኞ ሰኔ 10 ቀን ድረስ በኩባ እንደሚቆዩም ነው የተነገረው።
የሩሲያ የጦር መርከቦች በኩባ ምን ይሰራሉ?
“ፍሎቲላ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሩሲያ የባህር ኃይል ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት የባህር ኃይል መርከቦች መካከል የሚደረግ መደበኛ “የወዳጅነት”ጉብኝት አካል መሆኑን የኩባ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የሩሲያ ከሩሲያ ጦር መርከብ ጋ ወደ ካሪቢያን ያቀኑት መርከበኞችና የባህር ኃይሎ በካሪቢያ ቆይታቸው ወታደራዊ ልምምዶችን እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ወደ ኩባ ያቀኑት ግዙፍ ጦር ምርከቦች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተሸካሚዎች ናቸው። መርከቦቹ ቀደም ሲል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የሚሳኤል ልምምዶችን አከናውነዋል።
የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ መርከቦቹ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳልያዙ እና ለአምስት ቀናት የሚቆየው ጉብኝታቸው በአካባቢው ስጋት እንደማይፈጥር ተናግሯል።
ኩባ ይህንን ተበል እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች ግን የሩሲያ እንቅስቃሴ በትልቅ ስሌት የሚመራ መሆኑን እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን የአሜሪካ መሳሪያዎችን ተጠቅማ ሩሲያን እንድታጠቃ መፍቀዳቸውን ተከትሎ መልስ ለመስጠት እንደሆነ ተናግረዋል።
ሩሲያ ወደ ኩባ የላከቻቸው የጦር መርከቦቿ የትኞቹ ናቸው?
አድሚራል ጎርሽኮቭ፤ የሩሲያ ጦር መርከቦችን እየመራ ወደ ኩባ ያመራ ግዙፍ ጦር መርከብ ሲሆን፤ ሩሲያ ካሏት በጣም ግዙፍና ዘመናዊ ጦር መርከቦች ውስጥ አንዱ ነው።
መርከቡ ዚርኮን የተባለውን የረጅ ርቀት ሚሳዔልን ጨምሮ ካሊበር እና ኦኒክስ የተባሉ ክሩዝ ሚሳዔሎችን እንዲሁም የጸረ ሰርጓጅ መርከቦች ሚሳዔሎችን ታጥቋል።
ካዛን፤ ካዛን በኒውክሌር ኃል የሚሰራ ሰርጓጅ መርከብ ሲሆን፤ ካሊበር እና ኦኒክስ የተባሉ ክሩዝ ሚሳዔሎችን እንደታጠቀም ነው የተነገረው።
ፓሺን የተባለ ነዳጅ ጫን መርከብ እንዲሁም
ኖኮላይ ቺከር የተባለ በአደጋ ጊዜ መርከቦችን መጎተት የሚችል መርከብም ወደ ኩባ ካቀኑት መካከል ናቸው።
አሜሪካ የሩሲያ የጦር መርከቦች ኩባ መግባታቸውን ተከትሎ ምን አለች?
የአሜሪካ ባለስልጣናት “የሩሲያ የጦር መርከቦቸን ወደ ኩባ ማቅናት የሁለቱ ሀገራ መደበኛ የባህር ኃይል ግንኙነት አካል ነው፤ በአሜሪካ ላይ የሚፈጥረው ስጋ የለም” በሚል በይፋ አጣጥለውታል።
የዋይት ኃውስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ባሳለፍነው ረቡዕ ለመገናኛ ብዙሃ በሰጡት መግለጫ፤ የባህር ኃይሉ እንቅስቀሴ የመደበኛ ልምምድ አካል ነው፤ ሩሲያ ለኩባ ሚሳዔሎች አሳልፋ እንደመትሰጥ ምንም ምልክት የለም ብለዋል።
ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ ሀገሪቱ ቀደም ብላ የጦር መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን ባር ላይ በማሰማራት የመርከቦቹን እንቅስቃሴ በትኩረት እየተከታተለች ትገኛለች ተብሏል።