ዩክሬን ከጦር ግንባር 600 ኪሎሜትር ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቃ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች
ዩክሬን ሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ በመግባት ሱ-57 የተባለውን ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን መምታቷን ገለጸች
ይህ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ እና ጀርመን ዩክሬን በለገሷት የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሩሲያ ውስጥ የሚገኙ ኢላማዎችን እንድትመታ ይሁንታቸውን ከቸሯት በኋላ ነው
ዩክሬን ከጦር ግንባር 600 ኪሎሜትር ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቃ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች።
ዩክሬን፣ ጦሯ ከግንባር 600 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የጦር ሰፈር የነበረን የሩሲያ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን መምታቷን በትናንትናው እለት አስታውቃለች።
የኪቭ ዋነኛ የደህንነት ወይም ኢንተሊጀንስ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው ቪዲዮ አጋርቷል።ይህ የሚረጋገጥ ከሆነ ዩክሬን ሞስኮ በምትመካበት ባለሁት ሞተር ሱ-57 ስቲልዝ ጄት ላይ ያደረሰችው የመጀመሪያው ጥቃት ይሆናል ተብሏል።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ዋና ኢንተሊጀንስ ዳሬክቶሬት መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ጥቃቱ ከግንባር 589 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አክቱቢኒስክ ጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመው ባለፈው ቅዳሜ ነው።
ጥቃት የደረሰበት አውሮፕላን ስቲልዝ ሚሳይሎችን ተሸክሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ይዞ የሚበር እና ሞስኮ ከታጠቀቻቸው መሳሪያዎች ውስጥ ልዩ የሚባለው ነው።
ባለፈው አመት የሞስኮ አየር ኃይል ከ10 በላይ ሱ- 57 የጦር አውሮፕላኖችን የተረከበ ሲሆን በ2028 የሚረከባቸው 76 እንዲሰሩ አዟል።
የዩክሬን ወታደራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ አንድሪ ዩሶቭ በጥቃቱ በጦር ሰፈሩ ቆመው የነበሩ ሁለት ሱ-57 አውሮፕላኖች ጉዳት ሳይደርስባቸው እንደማይቀር መናገራቸውን ኤፒ የዩክሬን ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዘግቧል።
የዩክሬን አየር ኃይል ቃል አቀባይ ኢልያ የቭላሽ ባለፈው ሚያዝያ ወር ሞስኮ ሱ-57 ጄቾቿን የዩክሬን ጦር መሳሪያ ሊደርስ ከማይችልበት ርቀት ላይ አኑራለች ሲሉ ተናግረው ነበር።
ይህ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ እና ጀርመን ዩክሬን በለገሷት የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሩሲያ ውስጥ የሚገኙ ኢላማዎችን እንድትመታ ይሁንታቸውን ከቸሯት በኋላ ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ ያገኘቻቸውን ጦር መሳሪያዎች ሩሲያ ውስጥ ያለ ኢላማ ለመምታት እንድትጠቀም ከፈቀዱላት በኋላ ዩክሬን በሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እየመታች ነው።
ምዕራባውያን ዩክሬን በለገሷት የረጅም ርቀት መሳሪያዎች ሩሲያው ውስጥ ጥቃት እንድትፈጽም የሚፈቅዱ ከሆነ "በእሳት ይጫወታሉ" ሲሉ የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠንቅቀው ነበር።ይህ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ እና ጀርመን ዩክሬን በለገሷት የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሩሲያ ውስጥ የሚገኙ ኢላማዎችን እንድትመታ ይሁንታቸውን ከቸሯት በኋላ ነው።