የጋዜጠኛዋን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ንትርክ ምክንያት ፕሬዘዳንት ትራምፕ መግለጫቸውን በድንገት አቋረጡ
የጋዜጠኛዋን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ንትርክ ምክንያት ፕሬዘዳንት ትራምፕ መግለጫቸውን በድንገት አቋረጡ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ኤሲያዊ-አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የተነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ንትርክ ምክንያት ሲሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ በድንገት አቋርጠዋል፡፡
ትራምፕ ጋዜጠኛዋ ላነሳችው ጥያቄ “ቻይናን ጠይቂ “ የሚል መልስ ከሰጡ በኋላ ከሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
የሲቢኤስ ዜና የኋይት ሀውስ ዘጋቢ የሆነችው ጋዜጠኛ ዌይጃ ጂያንግ ከ80000 በላይ አሜሪካውያን በሞቱበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን ለምን እንደ አለምአቀፍ ውድድር እንደሚያዩት ፕሬዘዳንቱን ጠይቃለች፡፡
ትራምፕ ቻይና ተወልዳ በሁለት አመቷ ወደ አሜሪካ ለመጣችው ጋዜጠኛ “ያንን ጥያቄ ቻይናን ነው መጠየቅ ያለብሽ፣ ቻይናን ጠይቂ፤ እሽ”ብለዋታል፡፡
ትራምፕ ይህን ካሉ በኋላ ወደ ሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ለማለፍ ሞክረው ነበር፤ነገርግን ጂያንግ በተከታይ ጥያቄ ትራምፕን አቋረጠቻቸው፡፡
“ጌታው፣ ያንን በተለየ ለምን እኔን አሉኝ” በማለት በትራምፕ የተገረመችው ጂያንግ ጠየቀች፡፡
“እየነገርኩሽ ነው” ትራምፕ ይመልሳሉ፡፡ “ይህን በተለየ ለማንም አልናገርም፡፡ አስቀያሚ ጥያቄ ለሚጠይቅ ለማንም እመልሳለሁ” ብለዋል፡፡
“ይህ አስቀያሚ ጥያቄ አይደለም” ስትል ጂያንግ መልሳለች፡፡ “ምን ችግር አለው?”
በዚህ ጊዜ ትራምፕ ከሌላ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል እየሞከሩ ነበር፡፡
ጂያንግ ተከታይ ጥያቄ እንድትጠይቅ የፈቀደላት የሲኤንኤን ዘጋቢ የሆነው ኮሊንስ ወደ ማይክራሮኑ ተጠጋ፡፡
“ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ” አለ ኮሊንስ፡፡
“አይሆንም፤ ይበቃል” ብለው ትራምፕ መለሱ
“ነገርግን ወደ እኔ ነበር የጠቆሙት፤ ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ” ፕሬዘዳንት፡፡ “ጠርተውኛል፡፡”አለ ኮሊንስ፡፡
“ጠርቸህ ነበር፤ አልመለስክም፡፡” “አሁን ከጀርባህ ያለችውን ወጣት ሴት እየጠራሁ ነው” አሉ ትራምፕ
“ባልደረባየ አንድትጨርስ ፈልጌ ነበር” አለ ኮሊንስ፡፡ “ጥያቄ መጠየቅ እችላሁ?”
ትራምፕ መግለጫውን አቋረጡት፡፡
ትራምፕ መግለጫ ከሚሰጡበት ሮዝ ጋርደን ከመውጣቸው በፊት ክቡራትና ክቡራን አመሰግናሁ አሉ፡፡
ትራምፕ ባሳዩት ባህሪይ ጠንካራ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል፡፡
አንዳንድ ተችዎች የትራምፕ ንግግር ዘረናም ነበር ብለዋል፡፡ ጂያንግበኋይት ሀወስ ዘረኛ የሆነ ንግግር ሲያጋጥማት የመጀመሪያዋ አይደለም፡፡
ጂያንግ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገችው ባለስልጣን ኮሮና ቫይረስን “ኩንግ ፉሉ” ሲል መስቷን በትዊተር ገፃ በመጋቢት ወር ጽፋ ነበር፡፡