ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የበለጠ ለህመም የሚጋለጡ ሆነው ወንዶች ለምን ቶሎ ይሞታሉ?
ወንዶች ከሴቶች አንጻር ለህመም አነስተኛ የመጋለጥ እድል ቢኖራቸውም ቶሎ እንደሚሞቱ ጥናት አመልክቷል
ራስ ምታት፣ ድባቴ እና የጀርባ ህመም ሴቶችን አብዝተው የሚያጠቁ ህመሞች ሲሆኑ የልብ እና አዕምሮ ህመም ደግሞ ወንዶችን ከሚያጠቁ ህመሞች መካከል ዋነኞቹ ናቸው
ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የበለጠ ለህመም የሚጋለጡ ሆነው ወንዶች ለምን ቶሎ ይሞታሉ?
በመላው ዓለም ያሌ ሴቶች በአማካኝ 74 ዓመት በህይወት ሲኖሩ ወንዶች ደግሞ በአምስት ዓመት አንሰው በ69 ዓመታቸው ህይወታቸው ያልፋል፡፡
ላንሴት ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ጥናት ማዕከል ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት ሴቶች ከወንዶች አንጻር ለህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡
በዚህ ጥናት መሰረት ራስ ምታት፣ የጀርባ ህመም እና ድባቴ ሴቶችን አብዝተው የሚያጠቁ ህመሞች ናቸው ተብሏል፡፡
ይሁንና ወንዶች ከሴቶች አንጻር በተሻለ መልኩ ለህመም አይጋለጡም ቢባልም በምድር ላይ ግን አነስተኛ እድሜ እንደሚያሳልፉ በዚሁ ጥናት ላይ ተገልጿል፡፡
ወንዶች በተለይም ቴስቴስትሮን የተሰኘው ሆርሞን በወጣትነታቸው ጊዜ ጠንካራ እና ጤናማ እንዲሆኑ ቢረዳቸውም እየቆየ በሄደ ቁጥር ግን ለተለያዩ ጽኑ ህመም እንደሚያጋልጣቸው በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ወንዶች የሚያጋጥሟቸውን የጤና እክሎች የሚያስታግሱበት መንገድ ከሴቶች አንጻር ሲነጻጸር ራሳቸውን የሚጎዳ ነውም ተብሏል፡፡
በአብዛኛው ወንዶች የአዕምሮ ህመም፣ የትራፊክ አደጋ፣ ልብ ህመም፣ አልኮልን ጨምሮ ሲጋራ እና መሰል እጾች ህይወታቸው አጭር እንዲሆን ከሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
ረጅም ሰዎች ከአጭሮች የበለጠ ለአደጋዎች እና የጤና እክሎች ተጋላጭ ናቸው የተባለ ሲሆን በአብዛኛው ወንዶች ከሴቶች አንጻር በቁመት የበለጡ መሆናቸው ሌላኛው እድሜያቸውን ያሳጥራሉ ተብለው ከተዘረዘሩ ጉዳዮች መካከል ነው፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
በአራት ዓመት በፊት የተከሰተው እና ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የገደለው ኮሮና ቫይረስ ከሟቾች ውስጥ አብዛኞቹ ተጎጂዎች ወንዶች መሆናቸው አይዘነጋም፡፡
ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ጤናማ አመጋገብን የሚከተሉ እና ለጤናቸው ትኩረት መስጠታቸው ረጅም እድሜ እንዲኖሩ አስችሏቸዋል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት የልብ ምታቸው ዝግ እንዲል ያደርጋል የተባለ ሲሆን ይህም ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንስላቸዋል ተብሏል፡፡