1ሺ የሚያህሉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በ50 አውሮፕላኖች ታግዘው እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አድርገዋል
በደቡባዊ ስፔን በሚገኙ ተራሮች ላይ በተነሳው ሰደድ እሳት 2,000 ሰዎችን ከቤንሃቪስ ከተማ መሀል ለቀው እንዲወጡ አስገድዷቸዋል፤ ሶስት ሰዎች በአደጋው የመቁሰል አደጋ ደርሶባዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው እሳቱ የተነሳው በብሪታኒያ ቱሪስቶች በምትዘወተረው በሴራ ቤርሜጃ ተዳፋት ላይ ከኮስታ ዴል ሶል በላይ በሆነው በአንዳሉሺያ የባህር ዳርቻ አካባቢ ነው፡፡
ሞቃታማው የበጋ የአየር ጠባይ እና መጥፎ ንፋስ እሳቱን እያቀጣጠለ ነው ሲል ረቡዕ ረፋድ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ ገልጿል። ሰባት ሺ ሰዎች በሚኖሩባት ከተማ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ድንኳኖች ተተክለዋል፤ ነገርግን ከእሳት አደጋው የሸሹ አብዛኞቹ ሰዎች ከዘመዶቻቸው ዘንድ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡
ከመምሪያው ውስጥ እስከ 200 የሚደርሱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከ100 ወታደራዊ ሰራተኞች እና 50 የእሳት አደጋ ተከላካዮች ከሌሎች የኮስታ ዴል ሶል ከተሞች እሳቱን እየተዋጉ ነው።
የእሳት አደጋ የሚጋኙ አውሮፕላኖች ሐሙስ እለት መጀመሪያ ላይ በአካባቢው ላይ ነበሩ፡፡
የአንዳሉሲያ ክልል ፕሬዝዳንት ሁዋንማ ሞሪኖ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "በሚያሳዝን ሁኔታ ከ INFOCA ውስጥ ሶስት የእሳት አደጋ ተከላካዮች በተለያየ ዓይነት የተቃጠሉ እና ከመካከላቸው አንዱ 25 በመቶ ሰውነቱ ተቃጥሎ ወደ ማላጋ ሆስፒታል መወሰዱን ማሳወቅ አለብን" ብለዋል፡፡
በመስከረም ወር ሌላ የሰደድ እሳት በዚያው ተራራ ላይ ወድቆ በትንሹ 7,780 ሄክታር (30 ካሬ ማይል) ደን እና ቁጥቋጦን ወደ አመድ መቀየሩ ይታወሳል፡፡ 1,000 የሚያህሉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በ50 አውሮፕላኖች ታግዘው እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አድርገዋል።