የአሜሪካ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል
የኬንያው ፐሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸው ከሩሲያ ነዳጅ ለመግዛተ ፍላጎት እንዳላት እና ለዚህም ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያቋረጡ መሆኑ ይታወቃል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ሀገራት ባደረጉት ጉብኘትት የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ ማስጠንቀቃቸውም ይታወሳል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ሀገራቸው ያሉትን አማራጮች ሁሉ እያጤነች ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
“አሁን ከሩሲያ ጋር ያለው የመንግስት ከመንግስት ግንኙነት አጀንዳ ተግባራዊ መደረጉን እቀጥላለሁ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም በሂደት የነዳጅ ዋናግነ የማረጋጋት ጉዞን ለመጀመር ያስችላል ብለዋል።
ፕሬዝዳት ዊሊያም ሩቶ አክለውም “እንደ ሀገር ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው” ሲሉም ተግናረዋል።
የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ መወደድን ተከትሎ ኬንያ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።
የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ባሳለፍነው ሳምንት የነዳጅ ድጎማነ ለማንሳት ያሳለፉትን ውሳኔ እንደማይቀለብሱ አስታውቀዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ባሳለፍነው ነሃሴ ወር ኡጋንዳን፣ ጋናን እና ኬፕቨርዴን በጎበኙበት ወቅት የአፍሪካ ሃገራት ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር እንዳለ መናገራቸው ይታወሳል።
ከፍተኛ ዲፕሎማቷ፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ ማስጠንቀቃቸውም አይዘነጋም።
“የአፍሪካ ሃገራት ነዳጅንና የነዳጅ ምርቶችን የሚገበያዩ ከሆነ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን መጣስ እንደሚሆን ነው አምባሳደሯ በወቅቱ የተናገሩት።