በዓለ ሲመቱ ላይ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ተገኝተዋል
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የአዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ በዓለ ሲመት በዛሬው እለት የበርካታ ሀገራት መሪዎች እና ኬንያውያን በተገኙበት በናይሮቢ ተካሂዷል።
በበዓለ ሲመቱ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመትን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ዲፕሎማቶች በተገኙበት ነው የተካሄደው።
በበዓለ ሲመቱ ላይም ባሳለፍነው ነሀሴ ወር በኬንያ የተካሄደውን ፐሬዳንታዊ ምርጫ አብላጫ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ቃለ መሃላውን ተከትሎም በተሰናባቹ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በተመራጩ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መካከል የስልጣን ርክክብ ተካሂዷል።
ዛሬ ቃለ መሐላ የፈጽሙት ሩቶ ላለፉት 10 ዓመታት የኡሁሩ ኬንያታ ምክትል ሆነው መስታቸው የሚታወስ ነው፡፡
እናም በአሁኑ የስልጣን ዘመናቸው ብዙ ክምር እዳ ያለባትን ሀገረ ኬንያ ከተዘፈቀችበበት እዳየምትወጣበትን መንገድ ይፈልጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ በ50.49 በመቶ በሆነ ድምስ ማሸነፉቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
የኬንያ የድንበር እና ምርጫ ኮሚሽን 5ኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶ መሆናቸውን ይፋ ቢያደርግም፤ በምርጫው ዋነኛ ተቀናቃኝ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱን እንደማይቀበሉ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።