የመርከቦችን የሀይል ምንጭ ከነዳጅ ወደ ታዳሽ ሀይል የመቀየር ስራ መጀመሩ ተገለጸ
ንፋስ ሀይል ለመርከቦች የሀይል አማራጮች እንዲሆኑ የሙከራ ስራ ተጀምሯል ተብሏል
የጭነት መርከቦች የመጀመሪያውን የሙከራ ጉዞ ከሲንጋፖር ወደ ብራዚል እና ዴንማርክ እንደሚያደርጉ ተገልጿል
የመርከቦችን የሀይል ምንጭ ከነዳጅ ወደ ታዳሽ ሀይል የመቀየር ስራ መጀመሩ ተገለጸ።
ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጉዳት እያስተናገደች ሲሆን የያዝነው ዓመት ምድራችን ከፍተኛ ሙቀት አስተናግዳለች።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሱ ካሉ ጉዳቶች መካከልም ድርቅ፣ ጎርፍ ፣ሙቀት መጨመር፣ የመሬት መንሸራተት እና ሌሎችም ዋነኞቹ ሲሆኑ አለማችን በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ጉዳቶችን እያስተናገደች ትገኛለች።
ወደ ከባቢ አየር በካይ ጋዝ ከሚለቁ ኢንዱስትሪዎች መካከል የመርከብ ትራንስፖርት ሲሆን ይህም የ2 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።
መርከቦችን የሚለቁጥን በካይ የካርበን ጋዝን ለመከላከል የሀይል አማራጫቸውን ከነዳጅ ወደ ታዳሽ ሀይል እንዲቀይሩ ጥረቶች ተጀምሯል ተብሏል።
ዊንድዊንግስ የተሰኘ ኩባንያም መርከቦች በንፋስ ሀይል እንዲሰሩ የሚያደርግ የሙከራ ጉዞ በቻይና መጀመሩን አስታውቋል።
ዊንድ ዊንግ ኩባንያ ዋና መቀመጫውን እንግሊዝ በማድረግም በሚትስቡሺ መርከብ የመጀመሪያውን ጉዞ ከሲንጋፖር ወደ ብራዚል እና ዴንማርክ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
መርከቦች የንፋስ ሀይልን ከተጠቀሙ 30በመቶ የአየር ንብረት ጉዳትን መቀነስ እንደሚቻልም ተገልጿል።
ከዊንግዊንድ ኩባንያ በተጨማሪም የብሪታንያው ባር ቴክኖሎጂ ኩባንያ የመርከብ ትራንስፖርት አማራጭ የሀይል ምንጭ እንዲኖራቸው በሙከራ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
የንፋስ ሀይል ከውሀ ሀይል በመቀጠል ርካሽ ተብሎ የሚጠራ የሀይል ዘርፍ ሲሆን ለመርከብ ትራንስፖርት እንደ አማራጭ የሀይል ምንጭ ተይዟል።