ስርቆቱን በፈጸሙ አካላት ላይ ክስ የተመሰረተ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ ቤተሰቦች በእስር እንድትቀጣ ይፈልጋሉ ተበሏል
40 ሺህ ዶላር የተሸጠው የፕሬዝዳንት ባይደን ሴት ልጅ ማስታወሻ፡፡
ኤሚ ሀሪስ የተሰኘችው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሴት ልጅ አሽሊ ባይደን ጓደኛ ስትሆን በቤታቸው በእንግድነት ባደረችበት ዕለት ስርቆት ፈጽማ ሄዳለች ተብሏል፡፡
ይህች የፕሬዝዳንቱ ሴት ልጅ ጓደኛ የተባለች እንስት የሰረቀችውን የአሽሊ ባይደንን ዳየሪ ወይም ዕለታዊ ማስታወሻ አሳልፋ እንደሸጠችው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአሽሊ ባይንን ማስታወሻ የገዛው ተቋምም ወግ አጥባቂ ነው የተባለ ሲሆን በማስታወሻው ላይ የሰፈሩትን ይዘቶች፣ ፎቶዎች እና ሌሎች ነገሮችን በ40 ሺህ ዶላር መግዛቱ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ማስታወሻውን የሰረቀችው የፕሬዝዳንቱ ልጅ ጓደኛ ከሌላ ተባባሪ ጋር በመሆን እንደሸጡ ለፍርድ ቤት ያመኑ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጥፋተኛ አድርጓቸዋል፡፡
በስርቆቱ እና ሽያጩ የተሳተፉት እነዚህ ሁለት ግለሰቦችም በእስራት እንዲቀጡ አቃቢ ህግ ለፍረድ ቤት የጠየቀ ሲሆን እስካሁን የእስር ውሳኔው አልተላለፈባቸውም ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአደባባይ መድረኮች ላይ ላለመውደቅ ልዩ ጫማ ማድረግ ጀመሩ
የአሽሊ ባይደን ጓደኛ የልጅ ተንከባካቢ እንደሆነች እና ፍርድ ቤት መቅረብ አልቻልኩም በሚል ለፍርድ ቤት በማቅረቧ ምክንያት የፍርድ ውሳኔው ካሳለፍነው ነሀሴ ጀምሮ እስካሁን እንደዘገየ ተገልጿል፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን ቤተሰቦች እና ፍትህ ሚኒስቴር ግን ፍርድ ቤቱ ስርቆቱን በፈጸመችው እና እንዲሸጥ በተባበሩ አካላት ላይ የእስር ውሳኔ እንዲያስተላለፍ ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡
የአሽሊ ባይደን ማስታወሻን የገዛው ወግ አጥባቂ ድርጅትም የገዛቸውን መረጃዎች እስካሁን ለህትመት እንዳላበቃቸው ሲገለጽ በበይነ መረብ አማካኝነት እያሰራጫቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡