የሩሲያው ሜድቬዴቭ ባይደንን አሜሪካን አሳፋሪ "እብድ" ሲሉ ዘለፉ
ባይደን ከሁለት ሳምንት በፊት "እብድ" ሲሉ ለጠራቸው ፕሬዝደንት ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ "ወደ ኋላ አንልም" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል
የፑቲን ቀኝ እጅ ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ፕሬዝደንት ባይደን ራሳቸውን ከፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት ጋር የማነጻጸር መብት የላቸውም ብለዋል
የሩሲያው ሜድቬዴቭ ባይደንን አሜሪካን አሳፋሪ "እብድ" ሲሉ ዘለፉ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ቀኝ እጅ የሆኑት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ፕሬዝደንት ባይደን አሜሪካን የሚያሳፍሩ "እብድ" ናቸው፣ ራሳቸውን ከፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት ጋር የማነጻጸር መብት የላቸውም ብለዋል።
- ሩሲያ ባስወነጨፈችው ሚሳይል ዘለንስኪን እና የግሪኩን ጠ/ሚ ኢላማ አድርጋ ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣኑ ተናገሩ
- ምዕራባውያን ሩሲያ የኒዩክሌር ጦርነት እንድትጀምር እየገፋፏት ነው - ፑቲን
ፕሬዝደንት ባይደን በትናንትናው እለት ባሰሙት ንግግር፣ በ1941 ሩዝቬልት በኮንግረስ ፊት ቀርበው አሜሪካ ያልተጠበቀ የታሪክ እጥፋት ገጥሟታል ማለታቸውን አውስተዋል።
ባይደን የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸውን ዶናልድ ትራምፕን ለሩሲያ በስውር በመስራት ከሰዋል።
ባይደን ከሁለት ሳምንት በፊት "እብድ" ሲሉ ለጠራቸው ፕሬዝደንት ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ "ወደ ኋላ አንልም" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
"ምንም እንኳን ሩዝቬልት አቋም የለሽ የነበሩ ቢሆንም አሜሪካን ከቀውስ አውጥተዋታል። በሌላ መልኩ ባይደን እብድ እና የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ናቸው" ሲሉ የፕሬዝደንት ፑቲን የቀርብ ሰው እና የሩሲያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሜድቬዴቭ በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል።
ሜድቬዴቭ "ሩዝቬልት ሶቬት ህብረትን ጨምሮ ከአጋሮቻቸው ጋር ለሰላም ተዋግተዋል፤ ነገርግን ባይደን ሶስተኛውን የአለም ጦርነት ለመቀስቀስ ነቅተው እየሰሩ ናቸው" የሚል ክስ አቅርበዋል።
ሩዝቬልት ፋሽቶችን ተዋግተዋል፤ ነገርግን ባይደይ ለፋሽቶች እየተዋጉላቸው ነውም ብለዋል።
ከፈረንጆቹ 2008-12 ድረስ ሩሲያን በፕሬዝደንትነት የመሩት ሜድቬዴብ ጸረ-ምዕራባውያን የሆኑ የክሬሚሊን ጠበቃ ሆነዋል። የእሳቸው ንግግር የክሬሚሊን የበላይ አመራሮች ምን እንደሚያስቡ አመላካች መሆኑን ዲፕሎማቶች ይናገራሉ።