አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ያለመ ዘመቻ ጀመሩ
ሴቶቹ የክልከላ ዘመቻውን የጀመሩት ወንዶች ለዶናልድ ትራምፕ ድምጻቸውን ሰጥተዋል በሚል ነው
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻ ክልከላው ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ይቆያል ተብሏል
አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ያለመ ዘመቻ ጀመሩ፡፡
ባሳለፍነው ማክሰኞ የተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ አሁንም ዓለምን ትኩረት መሳቡን ቀጥሏል፡፡
የምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪዎች የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሀሪስ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ጽንስ ማቋረጥ ጉዳይ ዋነኛ የክርክር አጀንዳ ነበር፡፡
የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩዋ ካማላ ሀሪስ ጽንስ ማቋረጥ ጉዳይ የሰዎች መብት መሆን አለበት፣ ውሳኔው ለግለሰቦች መሰጠት አለበት በሚል ስትከራከር የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ይህ የሰዎች መብት ቢሆንም በጉዳዩ ዙሪያ መወሰን ያለባቸው ግዛቶች ናቸው የሚል አቋም አላቸው፡፡
ሁለቱም እጩዎች በጉዳዩ ዙሪያ አቋማቸውን ግልጽ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወንዶች እና የሀሳቡ ደጋፊ የሆኑ ሴቶች ድምጻቸውን ለዶናልድ ትራምፕ መስጠታቸውን ተከትሎ ምርጫውን አሸንፈዋል፡፡
ከባሏ ጋር ወሲብ በኮታ እና በክፍያ የምትፈጽመው ሚስት ትዳሯ እንዳይፈርስ ጠየቀች
የምርጫው ውጤት መታወቁን ተከትሎ የሴትነት አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች መብታችን ተነፍጓል በሚል ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ ሊጥሉ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻ ወንዶች ነጻነታችን ነፍገው በአካላችን መደሰት አይችሉም ሲሉም ጥሪያቸውን እንዳስተላለፉ ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
ከተላለፉ መልዕክቶች በተጨማሪም ሴቶች ለፍቅር አጋር መፈለጊያ ተብለው የለሙ የመገናኛ መተግበሪያዎችን ከስልካቸው ላይ እንዲያጠፉ እና ክልከላውም ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት እንዲቆይ የሚሉም ይገኙበታል፡፡
ከአሜሪካ ባለፈም መሰረቱን በደቡብ ኮሪያ ያደረገው “4ቢ” የተሰኘው የሴትነት ንቅናቄ የዶናልድ ትራምፕን መመረጥ መቃወሙን እና ዘመቻውን እንደተቀላቀለ አስታውቋል፡፡
“4ቢ” የተሰኘው ይህ ንቅናቄ የኮሪያ ቋንቋ አራት ቃላት የተፈጠረ ሲሆን ትርጉሙም የፍቅር ቀጠሮ አንይዝም፣ ልጅ አንወልድም፣ ወሲብ አንፈጽምም፣ አናገባም የሚል ትርጉም ያለው ነው፡፡