ከታራሚ ጋር ወሲብ የፈጸመችው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለች
ፖሊሷ ባለትዳር ነች የተባለ ሲሆን ቤተሰቦቿ በልጃቸው ድርጊት ማፈራቸው ተገልጿል
ከፖሊሷ ጋር ወሲብ የፈጸመው ታራሚ በስርቆት ወንጀል የታሰረ እና የ7 ወር ነፍሰጡር ፍቅረኛ ነበረው ተብሏል
ከታራሚ ጋር ወሲብ የፈጸመችው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
ዋንድስዎርዝ የተሰኘው እስር ቤት በእንግሊዝ የሚገኝ እድሜ ጠገብ ማረሚያ ቤት ነው፡፡
ከ170 ዓመት በፊት እንደተሰራ የሚገለጸው ይህ እስር ቤት በታራሚዎች የተጨናነቀ ነው የተባለ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ አንድ በዚህ እስር ቤት የምትሰራ ፖሊስ ከታራሚ ጋር ወሲብ ስትፈጽም የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቋል፡፡
የበርካቶችን ትኩረት የሳበው ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ ዘግይቶ በተደረገ ማጣራት የእስር ቤቱ ፖሊስ ከአንድ ታራሚ ጋር ወሲብ መፈጸሟን ያሳያል፡፡
ሊንዳ አብሩ የተሰኘችው ፖሊስ በእስር ቤቱ ውስጥ ባለ አንድ ስፍራ ከታራሚ ጋር ያልተገባ ድርጊት ፈጽማለች በሚል በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ፍርድ ቤት ቀርባም በስነ ምግባር ጥሰት ክስ ቀርቦባታል ተብሏል፡፡
ተንቀሳቃሽ ምስሉ በሌላ ታራሚ እንደተቀረጸ ሲገለጽ ይህ ታራሚም “ሰዎች እኛ ታሪክ እየሰራን ነው ነግሬያችኋለሁ” ሲል ይሰማል፡፡
የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር በኦንላይን በተለቀቀው ሀሰተኛ የወሲብ ቪዲዮ ምክንያት ካሳ ጠየቁ
በህግ ቁጥጥር ስር የዋለችው ፖሊስ አህት ለዴይሊ ሜይል እንዳለችው “እሷ ሁሌም ቢሆን ለየት ያሉ ነገሮችን ማድረግ ትወዳለች፣ ይህ ድርጊቷ ደግሞ ዋጋ እያስከፈላት ነው” ብላለች፡፡
እህታችን ባደረገችው ነገር ባሏን ጨምሮ ሁላችንም ቤተሰቦቿ አፍረናል ያለችው እህቷ በተፈጠረው ነገር ማዘኗን ተናግራለች፡፡
ከፖሊሷ ጋር ወሲብ የፈጸመው ታራሚ 82 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው ጌጣጌጦችን ሰርቋል በሚል ወንጀል ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ የአራት ዓመት እስር ተላልፎበት በእስር ላይ እንደነበር ሜይል ኦንላየን ዘግቧል፡፡
እንዲሁም ይህ ታራሚ የ7 ወር ነፍሰጡር ፍቅረኛ ነበረው የተባለ ሲሆን ፍቅረኛዋ በእስር ቤት የፈጸመው ተንቀሳቃሽ ምስልን ካየች በኋላ ጤናዋ መጎዳቱን እና ወደ ሆስፒታል ገብታለችም ተብሏል፡፡
ዋንድስዎርዝ የተሰኘው እስር ቤት በፈረንጆቹ 1851 የተሰራ እስር ቤት ሲሆን ሀገሪቱ ካሏት እስር ቤቶች መካከል በታራሚዎች የተጨናነቀ ነው ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፖሊሷን በቁጥጥር ስር ከማዋሉ ውጪ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት መቆጠቡ ተገልጿል፡፡