ማሪያ በፈረንጆቹ 2019 ምርመራ እንዲደረግ ፈልጋ የነበረ ቢሆንም፣ በኮኖና ወረርሽኝ እና በፔሌ የጤና ችግር ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል
የታዋቂው እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ ጠየቀች።
የታዋቂው ብራዚላዊ እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍራ እንዲወጣ እና የዲኤንኤ ወይም የዘረመል ምርምራ እንዲካሄድ ጠይቃለች።
ስካይ ኒውስ የብራዚል ሚዲያን ጠቅሶ እንደዘገበው ማሪያ ዶ ሶኮሮ አዝቬዶ የተባለች ሴት የፔሌ ስምንተኛ ልጅ መሆኗን እና ለልጆቹ ከሰጠው 60 በመቶ ሀብት ድርሻ እንደሚገባት ተናግራለች።
በሙሉ ስሙ ኢድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ በመባል የሚታወቀው ባለፈው ታህሳስ ወር ህይወቱ ያለፈው ፔል በንዛዜ ወቅት ስምንት ልጆች እና አንድ በአካል ያላገኛት ሴት ልጅ እንዳለችው ተናግሯል ተብሎ ይታመናል።
ፔሌ የአባትነት ምርምራ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆኖም፣ ምርመራው ሳይካሄድ በመሞቱ ምክንያት የማሪያ የህግ ጠበቃ አስከሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ ሊጠይቅ ችሏል።
ነገርግን የሶስት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፔሌን ባለቤት የወከለው ጠበቃ ጥያቄው "ምክንያታዊ ያልሆነ" እና "የማይሆን" ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ የተናገረችው ማሪያ እናቷ ማርገዟን ለፔሌ በፍጹም አልነገረችውም ብላለች።
ማሪያ በፈረንጆቹ 2019 ምርመራ እንዲደረግ ፈልጋ የነበረ ቢሆንም፣ በኮኖና ወረርሽኝ እና በፔሌ የጤና ችግር ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።
ከፔሎ ልጆች አንዱ የሆነው እና የውርስ ጉዳዩን በበላይነት የሚመራው ኢዲንሆ "ምርመራው ተካሂዶ እህታችን አለመሆኗ ተረጋግጧል" የሚል መልስ ሰጥቷል።