የፑቲን እናት ነኝ ያሉት ሴት በ97 አመታቸው ህይወታቸው አለፈ
ለረጅም አመታት የፑቲን ሚስጢራዊ እናት ነኝ የሚሉት ሴት በ97 አመታቸው መሞታቸውን ተዘግቧል
ፕሬዝደንት ፑቲን በዚህ ጉዳይ በግልጽ ተናግረው አያውቁም
የፑቲን እናት ነኝ ያሉት ሴት በ97 አመታቸአለፈ ህይወታቸው አለፈ።
ሴትዮዋ ከባለትዳር ወንድ ጋር በተፈጠረ የድብቅ ግንኙነት ማርገዛቸውን እና ቭላድሚር ፑቲን መውለዳቸውን ይናገራሉ።
ለረጅም አመታት የፑቲን ሚስጢራዊ እናት ነኝ የሚሉት ሴት በ97 አመታቸው መሞታቸውን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
ቬራ ፑቲን የተባሉት አኝህ ሴት ፕሬዝደንት ፑቲን ከባለትዳር ወንድ ጋር ግንኙት በማድረጋቸው የተወለዱ መሆናቸውን ይናገራሉ።
ፕሬዝደንት ፑቲን በዚህ ጉዳይ በግልጽ ተናግረው አያውቁም።
ሴትዮዋ እና ምናልባትም ፑቲንን ይመስላል ከተባለ የህጻን ጋር የተነሱት ፎቶ ሲዘዋወር ቆይቷል።
ቬራ በጣም ደሃ በምትባል በቀድሞ የሶቬት ግዛት በሆነችው ጆርጂያ ሲኖሩ ነበር።
ሴትዮዋ ፑቲን ልጄ ነው ሲሉ መናገር የጀመሩት በፈረንጆቹ 1999 ጀምሮ ቢሆንም ፕሬዝደንት ፑቲን ከእናታቸው ማሪያ እና ከአባታቸው ቭላድሚር በሴንትፒተርስበርግ መወለዳቸውን ጹፈዋል።
ፑቲን ሁለቱም ወላጆቻቸው በ1990 ዎቹ በካንሰር ህመም መሞታቸውን ተናግዋል። ነገረግን የፕሬዝንት ፑቲንን የልጅነት ታሪክ ማወቅ አስቻገሪ ነው የሚለው ዘገባው ቬራ ወደ አይቶቹ ከላኩት በኋላ ፑቲነሰ እንተቀየማቸው ይገልጻሉ።
በዚህ ሳምንት ህይወታቸው ያለፈው ቬራ ፑቲንን ለ60 አመታት ያህል ሳያገኙት ቆይተዋል።
በእርጅና ምክንያት የሞቱት ቬራ በትውልድ መንደራቸው መትኪ ተቀብረዋል።
የቀድሞ የሩሲያ የስለላ ተቋም ኬጂቢ አባል የነበሩት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ እስካሁን ሩሲያን በፕሬዝደንትነት እየመሩ ናቸው።
ፑቲን የአለምን ትኩረት የሳበውን እና ሀገራትን በሁለት ተቃራኒ ጎራ ያሰለፈውን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር የጀመረችውን ጦርነት እየመሩ እመሩ ነው።