ግጭት ባለባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉት ሴቶች “ሊታሰብ የማይቻል አሰቃቂ አደጋ ደርሶባቸዋል”- የተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊ
በሴቶች ላይ በተፈጸመና በሰማሁት የመደፈር ታሪክ “እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም” ብለዋል አሚና መሃመድ
የተመድ ሁለተኛዋ ሰው አሚና መሃመድ በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ ለተፈጸመው ሁሉ "ያለ ጥርጥር ፍትህ እና ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል"ሲሉ ዝተዋል
የተመድ ምክትል ሃላፊ አሚና መሃመድ የኢትዮጵያ ግጭት በሴቶች ላይ ባደረሰው ከባድ ጉዳት እጅጉን መደንገጣቸውን ገለጹ፡፡
ምክትል ዋና ጸሃፊዋ ይህንን ያሉት ለአምስት ቀናት በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እና ሶማሌ ክልሎችን ያደረጉትን ጉብኝት በማስመለክት በትናትናው እለት በኒውዮርክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡
አሚና መሀመድ የትግራይ ግጭት ባስከተለውን አስከፊ መዘዝ የተጎዱቱን የኢትዮጵያ ሴቶች አግኝተው ማነጋገረቻውንና በሰሙት ታሪክ “እንባቸው መቆጣጠር እንዳቃጣቸው ገልጸዋል፡፡
አሚና መሃመድ ግጭት ባለባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉት ሴቶች “ሊታሰብ የማይቻል አሰቃቂ አደጋ አጋጥሞቸዋል”ም ብለዋል።
በተለይም በጦርነቱ ወቅት የአስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸውን ታሪክ ማድመጥ ኩፉኛ የሚያምና የሚያስለቅስ ጉዳት መሆኑን በመግለጫቸው አንስቷል፡፡
"ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሊታሰብ በማይቻል መልኩ ተጎድተዋል"ም ብለዋል አሚና መሐመድ።
በልጆቻቸው ፊት ከተደረፈሩት ባሻገር የደረሰባቸውን ጉዳት የማያስታውሱ ሴቶችንም ጭምር ማግኘታቸውንም ተናግሯል ምክትል ዋና ጸሃፊዋ፡፡
አሚና መሀመድ በትግራይ አንዲት በተደጋጋሚ በቡዱን የተደፈረች፣ በዚህም ወንድ ልጅ የወለደችና አሁን ላይ የቤተሰቦቿንና ማህበረሰቡ አይን ማየት ተስኗት ራሷን አግላ የምትገኝ እንስት አግኝተው አሳዛኝ ታሪክ መስማታቸውንም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የአብሮነት ጉዞ ነበር ያሉት አሚና መሃመድ፤ ተመድ በተለይ ለሴቶች እና ህጻናት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማገገም አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ቅድሚያ መስጠቱን ይቀጥላል ሲሉም በትዊትር ገጻቸው ጽፈዋል፡
የተመድ ሁለተኛዋ ሰውና የቀድሞ የናይጄሪያ ሚኒስትሯ አሚና መሃመድ በጦርነቱ ከተጎዱት ሴቶች ባሻገር የኢትዮጵያን ጦርነት በተመለከተ ከትግራይ ክልል መሪዎች፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውንም ተናግረዋል።
ለተፈጸመው ግፍ ሁሉም ተጠያቂ ነው ያሉት አሚና መሐመድ "አንድ አካል በሌላው ላይ እንዲህ ማድረጉ ፍጹም ተቀባይነት የለውም" ሲሉም አስጠንቅቋል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ለተፈጸመው ሁሉ "ያለ ጥርጥር ፍትህ እና ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል"ሲሉ የተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊዋ አሚና መሃመድ ተናግረዋል።አሚና መሃመድ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ሳይታረቁና ተጠያቂ ካልሆኑ ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንደማይችልም አስረግጠው ተናግሯል፡፡
ምክትል ዋና ጸሃፊዋ እንደፈረንጆቹ በ2020 በትግራይ ክልል ግጭት ከተከሰተ በኋላ ኢትዮጵያን የጎበኙ ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ናቸው።