
የፓሪስ ኦሎምፒክ ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል
ነፍሰ ጡሮቹ ተፋላሚዎች በፓሪስ ኦሎምፒክ
በየ አራት አመቱ አንዴ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በፓሪስ ሲካሄድ 15ኛ ቀኑን ይዟል።
206 ሀገራት በሚሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶችም እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
ሀገራት ከውድድሩ ተሳትፎ የዘለለ ስኬት ማስመዝገብ የሚፈልጉ ሲሆን ዋናው ደግሞ ሜዳሊያዎችን በማንሳት የሀገራቸውን ስም በዓለም አደባባይ ማስተዋወቅ ነው፡፡
አንድ ቀን ብቻ በቀረው በዚህ ውድድር ላይ ለየት ያሉ ክስተቶች በብዙሃ መገናኛዎች ሽፋን እያገኙ ናቸው፡፡
ከዚህ መካከል በውድድሩ ላይ ለሀገራቸው ሜዳሊያ ለማምጣት እየተፋለሙ ያሉ ነፍሰጡር ስፖርተኞች የመኖራቸው ጉዳይ ነው፡፡
ግብጻዊቷ የሻሞላ ስፖርተኛ ናዳ ሃፌዝ አንዷ ስትሆን ይህች ስፖርተኛ የሰባት ወር ነፍሰጡር መሆኗ ታውቋል፡፡
የፓሪስን ጨምሮ ባለፉት ሶት ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ግብጽን በመከል የተወዳደረችው ይህች ስፖርተኛ ከውድድሩ በጊዜ ተሰናብታለች፡፡
በፓሪስ ኦሎምፒክ ያለ ፈቃዷ ዳሌ የነካው ግብጻዊ ስፖርተኛ ለእስር ተዳረገ
ስፖርተኛዋ በኢንስታግራም ገጿ ላይ ባጋራችው መልዕክት በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የሰባት ወር ነፍሰጡር ሆና መካፈሏን ተናግራለች፡፡
ሌላኛዋ ነፍሰ ጡር ሆና በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈችው የአዛርባጂያኗ የቀስት ስፖርተኛዋ ያይላጉል ራማዛኖቫ ነች፡፡
ያይላጉል በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የስድስት ወር ከ15 ቀናት ነፍሰጡር ሆና የተወዳደረች ሲሆን ልጁ ሆዴን እየረገጠችኝ ነበር የተወዳደርኩት ብላላች፡፡
ነፍሰጡር ስፖርተኞች በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሲሳተፉ የፓሪሱ የመጀመሪያ ያልሆነ ሲሆን በ2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ውድድር ላይ አሜሪካዊቷ የእጅ ኳስ ስፖርተኛ ኬሪ ዋልሽ አንዷ ነበረች፡፡
ይህች ስፖርተኛ ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን የእጅ ኳስ የወርቅ ሜዳሊያ ለአሜሪካ አስገኝታለች፡፡
የሕክምና ባለሙያዎች ነፍሰጡር ሴቶች ከባድ እንቅስቃሴ ማድረግ ጽንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶች እንዲደርሱ ሊያደርጉ ስለሚችሉ እንዲጠነቀቁ ያሳስባሉ፡፡