የስካንዲቪዲያን ሀገራት ትኩረታቸውን ከእንጨት ወደሚሰሩ ህንጻዎች በማድረግ ላይ ናቸው ተብሏል
በዓለማችን ከእንጨት ብቻ የሚሰሩ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።
በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የዓለም አየር ንብረት ለመከላከል ሀገራት የተለየ ትኩረት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ አንዱ ከእንጨት የሚሰሩ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን መገንባት ዋነኛው ነው።
ይህ ቴክኖሎጂ በስካንዲቪዲያን ሀገራት እየተለመደ ሲሆን ስዊድን፣ ፊንላንድ፣ ኖርዌይ እና ሌሎችም ሀገራት ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን ከእንጨት በመስራት ላይ ናቸው።
ስዊድን በዋና ከተማዋ ስቶኮልም አቅራቢያ ራሱን የቻለ ከእንጨት የተሰሩ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ያሉት ከተማ በመገንባት ላይ ስትሆን ይህ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሏል።።
ሙሉ ለሙሉ ከእንጨት የሚሰሩ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በራሳቸው ዛፎችን በመቁረጥ የሚሰሩ ቢሆንም እነዚህ ህንጻዎች ከብሎኬት እና ሌሎች ቴክኖሎጂችን በመጠቀም ከሚሰሩ ህንጻዎች ጋር ሲነጻጸሩ ወደ ከባቢ አየር የሚለቁት በካይ ጋዝ ግን የተሻለ እንደሆነ ተገልጿል።
በ50 ዓመታት የአየር ንብረት ልውጥ በዓለም ላይ ያስከተለው ጉዳት በአሃዝ
በዓለማችን በጣውላ ምርቷ የምትታወቀው ስዊድን ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከዓለማችን ሀገራት ቀዳሚዋ ስትሆን ከስዊድን በተጨማሪም ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ስዊዘርላንድ ሙሉ ለሙሉ ከእንጨት የተሰሩ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን በመስራት ላይ ናቸው ተብሏል።
አሁን ደግሞ እስያዊቷ ሲንጋፖር ከእንጨት ለተሰሩ ህንጻዎች ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥታለች የተባለ ሲሆን ከሁለት ወር በፊትም 468 ሺህ ስኩየር ጫማ ስፋት ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ አስመርቃለች።