አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ዝቅተኛው የተቀጣሪ ደመወዝ ለጊዜው 6 ሺህ 800 ብር መሆን አለበት- የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
ከመንግስትም ከግል ተቋማትም የተመረቁ ዜጎች የመንግስትና የባለሀብት እጅ የሚያዩ ሆነዋል ብለዋል የምጣኔ ሀብት ባለሙያው
የተሻለ ደመወዝ መክፈል ሴክተሮችንና ኩባንያዎችን ውጤታማ እንደሚደርግም ባለሙያው አቶ ሀሮን ጋንታ ተናግረዋል
ለሰራተኞች መከፈል ያለበት ደመወዝ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚሄድ ሊሆን እንደሚገባ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ሀሮን ጋንታ ይናገራሉ።
ከሰሞኑ “የኢኮኖሚ መዋዠቅ እና የስትራቴጂ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ ያስመረቁት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ሀሮን ጋንታ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ አሁን ለይ የኢትዮጵያ መንግስት የሚከፍለው ደመወዝ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር አብሮ እንደማይሄድ የገለጹ ሲሆን፤ ይህ በአስቸኳይ ሊስተካከል እንደሚገባ አንስተዋል።
መንግስት የተሻለ ደመወዝ መክፈል ሲጀምር የግል ድርጅቶች እና ሲቪል ማህበራትም ይህንኑ ፈለግ እንደሚከተሉ ያለሱት አቶ ሀሮን፤ አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ዝቅተኛው የተቀጣሪ ደመወዝ ለጊዜው 6 ሺህ 800 ብር መሆን እንዳለበት አንስተዋል።
ይህንን ቁጥር ያስቀመጡት ጥናቶችን በማጣቀስና ተጨማሪ ጥናቶችን በማካተት እንደሆነም አንስተዋል።
ለሰራተኞች መከፈል ያለበት ደመወዝ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚሄድ ሊሆን እንደሚገባ አቶ ሃሮን ተናግረዋል።
የተሻለ ደመወዝ መክፈል ሴክተሮችን እና ኩባንያዎችን ውጤታማ እንደሚደርግም ነው የምጣኔ ሀብት ባለሙያው የተናገሩት።
አሁን ላይ የሚከፈለው ደመወዝ ከመሰረታዊ ወጪዎች ጋር መመጣጠን እንደሚገባውም ባለሙያው ከአል ዐይን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ሀሮን ጋንታ አክለውም ከመንግስት እና ከግል ተቋማት የሚመረቁ ዜጎች የፈጠራ ባለቤቶች ከመሆን ይልቅ የመንግስትና የባለሀብት እጅ ጠባቂ እየሆኑ መምጣቱንም ይናገራሉ።
ብዙዎች የተማሩትን ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ በቀጥታ ወደ ቅጥር እንደሚመጡም ነው አቶ ሀሮን ለአል ዐይን የተናገሩት።
ባለሙያው፤ መንግስትም ብዙዎችን ከመቅጠር ይልቅ አነስተኛ ቁጥር ያለውን በመቅጠር የተሻለ ስራ እንዲሰራ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከመንግስትም ከግልም ተቋማት የሚመረቁ ወጣቶች ቁጥር ከ100 ሺህ እንደሚበልጥ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።