በአውሮፓ እና እስያ የአዛውንቶች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ተባለ
ጃፓን፣ ጀርመን እና ፊንላንድ በአዛውንቶች ቁጥር ቀዳሚ ሀገራት ናቸው
ሀገራቱ ዜጎቻቸው ልጆች እንዲወልዱ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ናቸው
በእስያ እና አውሮፓ የአዛውንቶች ቁጥር በፍጥነት እያደገ ነው ተባለ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች የወጣቶቻቸው ቁጥር የቀነሰባቸው የአውሮፓ እና እስያ ሀገራት ዜጎቻቸው ልጆች እንዲወልዱ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
በሁለቱ አህጉራት ያለው የውልደት ምጣኔ ዝቅተኛ ነው የተባለ ሲሆን በዛው ልክ ደግሞ እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ የሆናቸው ዜጎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጃፓን ከጠቅላላ ህዝቧ 29 በመቶው አዛውንቶች ሲሆኑ ጀርመን 23 በመቶ እንዲሁም ፊንላንድ ደግሞ በ22 በመቶ ሶስተኛዋ የአዛውንቶች ሀገር ተብላለች፡፡
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር የሚባለው አውሮፓ በአዛውንቶች ብዛት ቀዳሚ ሲሆን በመቀጠልም እስያ ደግሞ ሁለተኛው አህጎር ሆኗል፡፡