የዓለም ኩባንያዎች በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ሊከስሙ እንደሚችሉ ተገለጸ
የዓለም ስራ አስፈጻሚዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋነኛ ስጋታቸው እንደሆነ ተናግረዋል
የኩባንያዎች ዓመታዊ ትርፍ የ40 በመቶ ቅናሽ ሊያሳይ እንደሚችልም ተገልጿል
የዓለም ኩባንያዎች በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ሊከስሙ እንደሚችሉ ተገለጸ፡፡
ፒደብሊውሲ የተሰኘው ዓለም አቀፉ የቢዝነስ አማካሪ እና ጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናት የዓለም ኩባንያዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ዋነኛ የሕልውና ስጋት አድርገው እንደሚመለከቱት ተናግረዋል፡፡
በ101 የዓለም ሀገራት ውስጥ ያሉ ከ 4 ሺህ 700 በላይ የኩባንያዎችን ስራ አስፈጻሚዎች የተሳተፉበት ይህ ጥናት በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህ ጥናት መሰረትም አብዛኞቹ የኩባንያዎች ስራ አስፈጻሚዎች ድርጅታቸው በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ህልውናው እንደሚያከትም ያምናሉ ተብሏል፡፡
የመጀመሪያዋ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዲጄ ስራ ጀምራለች
በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ 38 በመቶዎቹ የዓለም ኢኮኖሚ እያደገ ሊሄድ ይችላል ብለው ያምናሉ የተባለ ሲሆን የዘንድሮው ዓመት እድገታቸው ከ73 በመቶ ወደ 45 በመቶ ዝቅ ሊልባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም 45 በመቶ የጥናቱ ተሳታፊዎች ኩባንያዎቻቸው አይዘምኑም ብለው የሚያስቡ ሲሆን የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ማነስ እና የሰራተኞች እውቀት ማነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸውም ብለዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ሌላኛው የዓለም ስራ አስፈጻሚዎች በስጋትነት የሚያዩት ጉዳይ ነው የተባለ ሲሆን የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት፣ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት፣ የቀይ ባህር ትራንስፖርት መስተጓጎልም የኩባንያዎችን ትርፍ እንደሚጎዳም መናገራቸው ተገልጿል፡፡
የዓለም ባንክ የ2024 ዓመት እድገት ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት ሊመዘገብ እንደሚችል ማስጠንቀቁ አይዘነጋም፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ አብዛኞቹ የኩባንያዎች ስራ አስፈጻሚዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስራቸውን እንደሚያቀልላቸው ቢያምኑም ሰራተኞቻቸው ግን ይህ ቴክኖሎጂ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው አይውቁም ተብሏል፡፡