
ቻይና፣ አሜሪካ እና ሕንድ ከፍተኛ የፕላስቲክ ብክለት ያለባቸው ሀገራት ናቸው
በካይ ፕላስቲክ በማምረት ቀዳሚ የሆኑ ዓለማችን ኩባንያዎች እነማን ናቸው?
ባሳለፍነው ዓመት ውስጥ ብቻ 220 ሺህ ቶን ፕላስቲክ ምርቶች ወደ ምድር የተጣሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 68 በመቶ ያህሉ መልሶ ጥቅም ላይ አልዋለም ተብሏል፡፡
የፕላስቲክ ምርቶች ሳይበሰብስ በመሬት ውስጥ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የመቆየት አቅም አለው የተባለ ሲሆን በሚያርፍበት ቦታም አደገኛ ኬሚካሎችን በመልቀቅ የስነ ህይወት ጉዳት ያደርሳል፡፡
ዝነኛው የሀይል ሰጪ መጠጥ ከሆኑ መካከል ኮካኮላ እና ፔፕሲኮ ዋነኛ የበካይ ፕላስቲክ አምራች ኩባንያዎች ናቸው፡፡
ኮካኮላ ኩባንያ ብቻ በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን ፕላስቲክ ያመርታል የተባለ ሲሆን ኩባንያዎቹ በተወሰነ መንገድ ያገለገሉ ምርቶቻቸውን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የምግብ እና መዋቢያ ምርቶችን ለዓለም ገበያ የሚያቀርበው ዩኒሊቨር ሌላኛው በካይ ፕላስቲክ ምርቶችን ከሚያመርቱት ኩባንያዎች መካከል ዋነኛው ነውም ተብሏል፡፡