በህክምና የታገዘ ሞትን የፈቀዱ 10 የዓለማችን ሀገራት
ስዊዘርላንድ በህክምና የታገዘ ሞትን የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች

አሜሪካ ካሏት 50 ግዛቶች ውስጥ 10ሩ በህክምና የታገዘ ሞትን ይፈቅዳሉ
በህክምና የታገዘ ሞትን የፈቀዱ 10 የዓለማችን ሀገራት
በርካታ የዓለማችን ሀገራት መዳን በማይችሉ ህመሞች እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎቻቸው በህክምና ታግዘው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላቸው፡፡
የአውሮፓዋ ስዊዘርላንድ ከፈረንጆቹ 1942 ጀምሮ በህክምና የታገዘ ሞትን በመፍቀድ በዓለማችን የመጀመሪያዋ ሀገር ናት፡፡
ሀገሪቱ ይህን አገልግሎት በራስ ወዳድነት አመለካከት ምክንያት የማትሰጥ ሲሆን ሆላንድ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይም በህክምና የታገዘ ሞትን ከፈቀዱ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡
አሜሪካ ካሏት 50 ግዛቶች ውስጥ 10ሩ በህክምና የታገዘ ሞት አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ካሊፎርኒያ ፣ኮሎራዶ፣ ዋሸንግተን እና ኒው ጀርሲ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ እና መዳን በማይችል ህመም ለተጠቁ ታዳጊዎች ደግሞ በወላጆቻቸው ውሳኔ አማካኝነት በህክምና የታገዘ ሞት አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በህክምና የጣገዘ ሞት አገልግሎት በመፍቀድ የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ያደረጋትን አዋጅ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ ማጽደቋ ይታወሳል፡፡
በዚህ አዋጅ መሰረትም በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን እንዲቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
የዚህ ስርዓት አተገባበር መመሪያን በቀጣይ የጤና ሚኒስቴር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በማይድን ህመም የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመርዳት ያለመ እንደሆነ በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል፡፡