ኢኮኖሚ
ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ሉግዘምበርግ፣ ቤልጂየም እና ኔዘርላንድ በአማካኝ ከፍተኛ ወርሃዊ ክፍያ የሚከፍሉ ሀገራት ናቸው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/258-182448-photo-2025-02-10-17-24-33_700x400.jpg)
ሞሪሺየስ፣ ደቡብ አፍሪካ እና አልጀሪያ ከአፍሪካ ከፍተኛ ደመወዝ ከፋይ ሀገራት ናቸው
ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
የተሸለ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ለዜጎቻቸው ከሚያቀርቧቸው አገልግሎቶች ውስጥ ለሰራተኞቻቸው የሚያስቀምጡት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አንዱ ነው፡፡
በዚህም መሰረት አነስተኛ ህዝብ ብዛት ያላት ሉግዘምበርግ በአማካኝ 8 ሺህ ዶላር ወርሃዊ ደመወዝ በመክፈል ከዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ናት፡፡
የአውሮፓ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ቤልጂየም 7 ሺህ 500 ዶላር አማካኝ ወርሃዊ ደመወዝ ስትከፍል ኔዘርላንድ ደግሞ 7ሺህ 500 ዶላር ትከፍላለች፡፡
ኖርዌይ፣ ኦስትሪያ እና አሜሪካ ከአራተኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሀገራት ናቸው፡፡
ወደ አፍሪካ ስንመጣ ሞሪሺየስ በአማካኝ በወር 350 ዶላር ለሰራተኞቿ በመክፈል ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን ደቡብ አፍሪካ 260 ዶላር እንዲሁም ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ደግሞ 150 ዶላር በወር ለሰራተኞቿ እንደምትከፍል ፎርብስ ዘግቧል፡፡