ብዙ ቤተ መጽሀፍት ያላቸው ሀገራት
ሩሲያ፣ ፈረንሳይ እና ቸክ ሪፐብሊክ ብዙ ቤተ መጽሃፍት ያላቸው ሀገራት ናቸው
ሩሲያ እና ቻይና ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ቤተ መጽሃፍት አሏቸው
የስልጣኔ ምንጭ እንደሆነ የሚነገረው ማንበብ በተለይም ሀገራት ታሪካቸውን እና የዜጎቻቸውን ህይወት ለማሻሻል ምቹ ማንበቢያዎችን ይገነባሉ፡፡
የሚያነቡ ዜጎች ጠያቂዎች እና ለችግሮቻቸው ዘላቂ መፍትሔ በመፈለግም ይታወቃሉ፡፡
ሪሰርች ጌት የተሰኘው ዓለም አቀፍ የጥናት ማዕከል ብዙ ቤተ መጽሃፍት ያላቸው ሀገራትን ዝረዝር ይፋ አድርጓል፡፡
እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ቸክ ሪፐብሊክ ያላት ቤተ መጽሃፍት ከጠቅላላ ህዝቧ ጋር ሲነጻጸር በዓለም ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡
በአጠቃላይ በቤተ መጽሃፍት ብዛት ግን ሩሲያ፣ ፈረንሳይ ፖላድ እና አውስትራሊያ ቀዳሚ የዓለማችን ሀገራት ናቸው፡፡
የአሜሪካዋ ኒው ዮርከ ከተማ ብዙ ቤተ መጽሃፍት ቤት የሚገኝባት ከተማ ተብላለች፡፡