ዜጎቻቸው ዘግይተው ጋብቻ የሚመሰርቱባቸው ሀገራት
የኢስቶኒያ ወንዶች ዘግይተው ከሚያገቡ ሀገራት መካከል የመጀመሪያው ናቸው

ከአፍሪካ ናሚቢያዊን ወንዶች በአማካኝ በ34 ዓመታቸው ጋብቻ ይመሰርታሉ
ዜጎቻቸው ዘግይተው ጋብቻ የሚመሰርቱባቸው ሀገራት
ጋብቻ የሰው ልጆች ህይወት ምርጫዎች መካከል አንዱ ሲሆን ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ቀድመው አልይም ዘግይተው ጋብቻ ፈጽማሉ፡፡
ጋብቻን ሁሉም ዕምነቶች የሚያበረታቱት ተግባር ሲሆን ስርዓቱ ከሀገር ሀገር በተለያየ መንገድ ይፈጸማል፡፡
ስታትስቲካ ባወጣው መረጃ መሰረት የምስራቅ አውሮፓ እና እስያ ሀገራት ዘግይተው ጋብቻ ይፈጽማሉ የተባለ ሲሆን አፍሪካዊቷ ሞዛምቢክ ደግሞ በወጣትነታቸው ጋብቻ የሚመሰረትባት ሀገር ተብላለች፡፡
በኢስቶኒያ በአማካኝ የሀገሪቱ ዜጎች በ36 ዓመታቸው ጋብቻ ይመሰርታሉ የተባለ ሲሆን በሞዛምቢክ ግን በ23 ዓመታቸው ያገባሉ፡፡
ጣልያን፣ ስሎቬንያ እና ናሚቢያ በአማካኝ ዘግይተው ጋብቻ ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ባልና ሚስቶች በመካከለቻው ያለው የእድሜ ልዩነት በጋብቻ ዘላቂነት ላይ የራሱ አወንታዊ ሚና አለው፡፡