
ደቡብ ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ እና አፍጋኒታን ዝቅተኛ የባንክ አገልግሎት ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የባንክ አገልግሎት ዝቅተኛ የሆነባቸው የዓለማችን ሀገራት
የሰዎችን የዕለት ተዕለት ስራዎች ከሚያቀሉ ተቋማት መካከል አንዱ የሆኑት ባንኮች በመላው ዓለማችን ሀገራት በሚገባ አልተስፋፉም፡፡
እንደ ብሊምበርግ ዘገባ ከሆነ ከዓለማችን ስምንት ቢሊዮን ህዝብ ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ያህሉ አሁንም ከባንክ አገልግሎት ውጭ ናቸው፡፡
ጎረቤት ደቡብ ሱዳን የባንክ አገልግሎት ካልተስፋፋበው ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ ሀገር ስትባል ማዕከላዊ አፍሪካ እና አፍጋኒስታን ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሀገራት ናቸው፡፡
አፍሪካ ከሌላው አህጉር ባንክ ያልተስፋፋበት አህጉር ሲባል ኒጀር፣ ማዳጋስካር፣ ሴራሊዮን፣ሞሪታንያ እና ቻድ አገልግሎቱ ካልተስፋፋባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በዓለማችን በየዕለቱ በአማካኝ 7 ነጥብ 5 ትርሊዮን ዶላር የገንዘብ ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን የዓለማችን ቁጥር አንድ ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ዕለታዊ የገንዘብ ልውውጥ መጠኑ 300 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የስታትስቲካ መረጃ ያስረዳል፡፡