ከሁለት ሚሊዮን በታች ህዝብ ያላቸው የዓለማችን ሀገራት
አፍሪካዊቷ ሲሸልስ 130 ሺህ ህዝብ በመያዝ የመጨረሻው ሀገር ናት

ኬፕ ቨርዴ፣ ሉግዘምበርግ፣ ባህሬን እና ጅቡቲ በተመሳሳይ ከሁለት ሚሊዮን በታች ህዝብ ካላቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
ከሁለት ሚሊዮን በታች ህዝብ ያላቸው የዓለማችን ሀገራት
በዓለማችን 193 ሀገራት በይፋ የሀገርነት እውቅና ያገኙ ሀገራት ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ ከ50 በላይ የሆኑ ሀገራ ያላቸው ጠቅላላ ህዝብ ከሁለት ሚሊዮን በታች ነው፡፡
ሲሸልስ 130 ሺህ ህዝብ በመያዝ በዓለማችን ጥቂት የህዝብ ብዛት ካላት ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ ናት፡፡ ኢኮኖሚዋን ከቱሪዝም እና ግብርና ስራዎች የምትደጉመው ሲሸልስ 115 ደሴቶችን በመያዝ ተወዳጅ ሀገር ናት፡፡
ኬፕቨርዴ 526 ሺህ፣ ሉግዘምበርግ 673 ሺህ ፣ ኮሞሮስ 866 ሺህ እና ምስራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ ደግሞ አንድ ሚሊዮን 168 ሺህ ህዝብ በመያዝ ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ በታች ያላቸው ሀገራት ተብለዋል፡፡
ባሬን፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሞሪሺየስ እና ኢስቲኒያ ከሁለት ሚሊዮን በታች ካላቸው ሀገራት መካከል ሲሆኑ ሕንድ፣ ቻይና እና አሜሪካ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆኑ የዓለማችን ሀገራት ናቸው፡፡