ዓለም አቀፍ ውጥረት ለአፍሪካ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል ሲል አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ
የአፍሪካ ሀገራት ከ10 ዓመታት በኋላ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በአራት በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ትንበያ ተሰጥቷል
በዓለም አቀፍ ሽኩቻው የአፍሪካ ግማሹ ክልል ተጽዕኖ ሊደርስበት ይችላል ተብሏል
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወቅታዊ ውጥረቱ የዓለም ምጣኔ-ሀብትን ወደ ተቃራኒ ጎራ መከፋፈል ለአፍሪቃ ለዘለቄታዊ ጉዳት ሊደርስባት ይችላል ብሏል።
- አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ሲያደርገው የነበረው ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ገለጸ
- አይኤምኤፍ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት አዝጋሚ እድገት እንደሚያስመዘግቡ ተነበየ
አይኤምኤፍ "የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች እየተባባሰ ከሄደ፣ ሀገራት በከፍተኛ የገቢ ምርት የዋጋ መጨመር ሊመቱ ወይም ቁልፍ ገበያዎቻቸውን ሊያጡ ይችላሉ" በማለት አስጠንቅቋል።
የአህጉሪቱ ግማሹ ክልል ተጽዕኖ ሊደርስበት ይችላል ማለቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።
ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ከ10 ዓመታት በኋላ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርታቸው በአራት በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ገምቷል።
የውጭ የገንዘብ ፍሰቶችም ጫና ውስጥ ከገባ ጉዳቱ ሊባባስ ይችላል ሲል ድርጅቱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ይህም በረጅም ጊዜ የሀገራት የምጣኔ-ሀብት እደት ላይ ዘላቂ ጉዳት ያስከትላል ተብሏል።
የአይኤምኤፍ ሪፖርት ወደ ቀጣናው የሚገባው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሊቀንስ እንደሚችል ገምቷል።
"ሀገሮች የመቋቋም አቅም መገንባት አለባቸው። ይህን ማድረግ የሚቻለውም የተጀመረውን ቀጣናዊ የንግድ ትስስር በማጠናከር ነው" ሲል ምክረ-ሀሳብ አቅርቧል።
አይኤምኤፍ "የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን ማስፋት እና በውጪ ገቢዎች ላይ ከመጠን በላይ ጥገኝነትን መቀነስ" ያስፈልጋል ብሏል።