ከፍተኛ የደን ሽፋን ያለባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ዓለም ካላት ጠቅላላ የመሬት አካል 31 በመቶው በደን የተሸፈነ ነው
በደን ሽፋን ብዛት ብራዚል ቀዳሚ ስትሆን፤ ካናዳና ሩሲያ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል
ዓለማችን ካላት አጠቃላይ መሬት ውስጥ 31 በመቶ በደን መሸፈኑን በተባበሩት መንግስታት የግብርና እና የምግብ ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
ይህ የደን ሀብት በአየር ንብረት ለውጥ፣ በደን ምንጣሮ እና በሌሎች ምክንያች እየመነመነ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን፤ ለአብነትም ዓለማችን በፈረንጆቹ በ1990 የነበራት 33 በመቶ የደን ሽፋን በ2020 ወደ 31 በመቶ ዝቅ ብሏል።
እንደ ፋኦ ሪፖርት ቀጥለው የተዘረዘሩ ሀገራት ከፍተኛ የደን ሽፋን ያለባቸው ናቸው፤