የዓለም የባሎች ቀን በመከበር ላይ ይገኛል
በዓሉ መቼ መከበር እንደጀመረ ባይታወቅም በምዕራባዊያን ሀገራት ባልን ከስራ በማሳረፍ እና ስጦታ በመስጠት ይከበራል
በዓለማችን ካለው ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ ከ2 ቢሊዮን በላይ ይህሉ ያላገቡ ናቸው ተብሏል
የዓለም የባሎች ቀን በመከበር ላይ ይገኛል
የባሎች ቀን በየዓመቱ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 20 ላይ የሚከበር ሲሆን በዓሉ በብዛት ስጦታ ለባል በመስጠት፣ ከስራ በማሳረፍ ወይም እሱ የሚሰራውን ስራ ተክቶ በመስራት፣ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች ደስታ ሊፈጥሩ በሚችሉ ሁነቶች ይከበራል፡፡
መቼ ጀምሮ መከበር እንደጀመረ የማይታወቀው ይህ በዓል በተለይም ልጅ ያልወለዱ ባሎችን ወይም አባት ያልሆኑ ባሎችን ለማሰብ በሚል መከበር እንደጀመረ ይገለጻል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ የባል እና ሚስት ሃላፊነት እየተቀያየረ የመጣ ሲሆን ከዚህ በፊት ለኑሮ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መሸፈን የባል ግዴታ የነበረ ሲሆን ልጆችን መንከባከብ ጨምሮ የቤት ውስጥ ስራዎችን መከወን ደግሞ ለሴቶች የተሰጠ ግዴታ ነበር፡፡
ስትወሰልት የተያዘች ሚስት በባሏ እርዳታ የምትወደውን ሰው አገባች
እነዚህ ሀላፊነቶች አሁንም ያሉ ቢሆንም ወጪን በጋራ መሸፈን፣ ልጆችን መንከባከብ እና ሌሎች የቤት ውስጥ ስራዎችንም በጋራ መወጣት እየተለመደ መጥቷል፡፡
አፍሪካ ደቡብ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የሚያገቡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን አውሮፓ፣ ሩቅ ምስራቅ እና አሜሪካ ደግሞ ያላገቡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ የሆነባቸው አህጉራት ናቸው፡፡
ከዓለም ጠቅላላ ህዝብ 8 ቢሊዮን ያህል ውስጥ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ያህሉ ያላገባ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ 47 በመቶ ያህሉ ያገቡ እንደሆኑ ዓለም አቀፉ የህዝብ ብዛት ጥናት ተቋም ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ያላገቡ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት፣ ግለኝነት፣ ሀላፊነት የመውሰድ ፍላጎት ማጣት እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች የሚያገቡ ዜጎች ቁጥር እንዲቀንስ ያደረጉ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ይገለጻል፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፖሊሲ ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን ካለው 8 ቢሊዮን ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ ወንዶች ከሴቶች በ40 ሚሊዮን ብልጫ አላቸው፡፡
ይሁንና በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ደግሞ የጾታ አለመመጣጠን ያለ ሲሆን በተለይም በመካከለኛው መስራቅ ሀገራት ወንዶች ከሴቶች ያላቸው ልዩነት የሰፋ ሆኗል፡፡
ኳታር፣ ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የወንዶች ቁጥር ከሴቶቹ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ሲሆን ለነዚህ ሀገራት የጾታ አለመመጣጠን ዋነኛው ምክንያት ለስራ በሚል ከተለያዩ ሀገራው የሚገቡ ወንዶች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የህዝብ ፖሊሲ ጥናት ሪፖርት ያሳያል፡፡
ከአፍሪካ ኢኳቶሪያ ጊኒ እና ሲሸልስ ከፍተኛ የወንዶች ብዛት ያለባቸው ሀገራት ሲሆኑ አርመንያ፣ ዩክሬን፣ ቤላሩስ፣ ላቲቪያ፣ ዚምባብዌ እና ሩሲያ ደግሞ በተቃራኒው የሴቶች ህዝብ ብዛት ከፍተኛ የሆኑባቸው ሀገራት ናቸው፡፡