በዓሉ የሰራተኞችን ደህንነት ለማስከበር ያለመ ነው
የላብ አደሮች ወይም የሰራተኞች ቀን በሰራተኞች ላይ የሚደርስን የስራ ጫና ለመቀነስ የሚደረግን ትግል ለማሰብ ነበር እኤአ ከ1889 ጀምሮ መከበር የጀመረው።
በወቅቱ የኢንዱስትሪ መስፋፋትን ተከትሎ በሰራተኞች ላይ የሚፈጸሙ የተለያዩ በደሎችን ለማስቀረት ዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ንቅናቄ ተካሂዷል።
ይህንን ተከትሎም በዓሉ በሁሉም ሀገራት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
እንደ ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ወይም አይኤልኦ መረጃ ከሆነ የዓለም ሰራተኞች ብዛት 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ደርሷል።
በዓለም ላይ ካሉ ሰራተኞች ውስጥም 170 ሚሊዮን ያህሉ የስደተኛ ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።