ከ100 በላይ ሀገራት በፈረንጆቹ 2030 የደን ጭፍጨፋን ለማስቆም ቃል ገቡ
ይህን እቅድ ለማሳካት ከ19 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፍልግ ተነግሯል
ደኖች በግምት 30 በመቶ የሚሆነውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን ይቀበላሉ ሲል ለትርፍ ያልተቋቋመው የአለም ሀብት ኢንስቲትዩት አስታውቋል
ከ100 በላይ ሀገራት በፈረንጆቹ 2030 የድን ጭፍጨፋ በትናንትናው እለት ባካሄዱት ስብሰባ የደን ጭፍጭፋን ለመቀልበስና የመሬት ሽርሸራን በ10 አመቱ መጨረሻ ለማስቆም ቃል ገብተዋል፡፡ ይህን እቅድ ለማሳካት ከ19 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፍልግ ተነግሯል፡፡
በስኮትላንድ፣ እየተካሄደ ባለው ኮፕ26 ስብሰባ ላይ የወጣውን የጋራ መግለጫ የአለም 85 በመቶ የሚሆነው ደን የሚገኝባቸው ብራዚል፣ ኢንዶኔዥያና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ደግፈውታል፡፡
የግላስጎው የመሪዎች የደን እና የመሬት አጠቃቀም መግለጫ በድምሩ ከ13 ሚሊዮን ካሬ ማይል በላይ የሚሸፍኑ ደኖችን እንደሚሸፍን የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሪዎቹን ወክለው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የብሪታኒያ መሪ ቦሪስ ጆንሰን "የሰው ልጅ የረዥም ጊዜ ታሪክ እንደ ተፈጥሮ አሸናፊ ሆነን የማቆም እድል ይኖረናል" ብለዋል።
ለደን አልሚዎች እና ለዘላቂ እርሻዎች በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቃል ኪዳንን ጨምሮ በርካታ ተጨማሪ የመንግስት እና የግል ውጥኖች ግቡን ላይ ለመድረስ ማክሰኞ ተጀምረዋል።
ደኖች በግምት 30 በመቶ የሚሆነውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን ይቀበላሉ ሲል ለትርፍ ያልተቋቋመው የአለም ሀብት ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
“ደኖቹ ልቀትን ከከባቢ አየር ውስጥ በማውጣት የአየር ንብረትን እንዳይሞቁ ይከላከላሉ. ሆኖም ይህ የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተከላካይ በፍጥነት እየጠፋ ነው። ዓለም በ2020፣ 258,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ደን አጥታለች” ሲል የWRI የደን ጭፍጨፋ ክትትል ግሎባል ፎረስት ዎች አስታውቋል።
በስምምነቱ መሰረት ብሪታንያን ጨምሮ 12 ሀገራት የተራቆተውን መሬት ለመመለስ እና የሰደድ እሳትን ለመቋቋም የሚደረገው ጥረት ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ለመርዳት ከፈረንጆቹ2021 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ 8.75 ቢሊዮን ፓውንድ (12 ቢሊዮን ዶላር) የገንዘ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
የCOP26 ዓላማው የአለም ሙቀት መጨመርን በ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ (2.7 ፋራናይት) ከቅድመ-ኢንዱስትሪ ደረጃ በላይ የመቆጣጠር ግብን ለማስቀጠል ነው።