ስምምነቱ በቀረጥና ታክስ ጉዳዮች ላይ በመከሩት የቡድን 20 አባል ሀገራት ነው የተወሰነው
በጣሊያን መዲና ሮም የተሰባሰቡት የቡድን 20 አባል ሀገራት በግዙፍ ድንበር ተሻጋሪ ኩባያዎች ዝቅተኛ የቀረጥ መጠን ላይ መስማማታቸውን አስታወቁ፡፡
ሀገራቱ የግዙፍ ኩባያዎች ዝቅተኛ የቀረጥ መጠን 15 በመቶ እንዲሆን ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን የሀገራቱ ተወካዮች ገልጸዋል፡፡
የ100 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ድጋፍ” አለመፈጸማቸው ተቀባይነት የለውም- አፍሪካ ህብረት
ይህ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ዝቅተኛ ግብርን በሚያስከፍሉ ሃገራት እያደረጉ የሚጠበቅባቸውን ግብር ከመክፈል ይሸሹ የነበሩ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ጭምር የሚጠበቅባቸውን እንዲከፍሉ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት ያለን፤ የቡድን 20 አባል ሀገራት በሮም ለሁለት ቀናት ባደረጉት ውይይት “ታሪካዊ” የተባለውን የቀረጥ መጠን 15 በመቶ እንዲሆን ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ይህ የማሻሻያ ዕቅድ በ 140 ሀገራት መደገፉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ዩኤኢ በአየር ንብረት ለውጥ መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዝቅተኛ የታክስ ውሳኔው 15 በመቶ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱ ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነ በመግለጽ “ጨዋታ ቀያሪ ውሳኔ ነው” ብለውታል፡፡ 80 በመቶ የዓለምን ጥቅል የሀገር ውስጥ ገቢ የሚሸፍኑት ሀገራቱ ያደረጉት ስምምነት ከቀረጥ ስምምነት ያለፈ ትርጉም እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡
የስልጣን ጊዜያቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙት የጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ውሳኔው ትልቅ ስኬት መሆኑን ሲገልጹ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት ያለን ደግሞ ውሳኔው “ታሪካዊ” እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሜርክል፤ የዓለም ማህበረሰብ የግዙፍ ኩባንያዎች ዝቅተኛ የታክስ መጠን 15 በመቶ እንዲሆን ተስማምቷል ብለዋል፡፡ በመሪዎቹ ስምምነት የተደረሰበት ይህ የታክስ መጠን በአውሮፓውያኑ 2023 ስራ ላይ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡
ሆኖም ሃገራቱ ምንም እንኳን በቀረጥ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ቢደርሱም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮ ላይ ግን ለመስማማት አልቻሉም፡፡
የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በስኮትላንድ ግላስኮው ሊጀመር የቀናት እድሜ ብቻ ቀርተውት ሳለ ይህ መሆኑ ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡