ለረጅም አመታት ስልጣን ላይ ያሉ የሀገራት መሪዎች
ኢኳቶሪያል ጊኒን ከፈረንጆቹ 1979 ጀምሮ በመምራት ላይ የሚገኙት ቲወዶር ኦቢያንግ ለ44 አመት በስልጣን ላይ ናቸው
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ለረጅም አመት ሀገራቸውን በመምራት ላይ ከሚገኙ 10 መሪዎች መካከል ተካተዋል
በምርጫም ሆነ በሃይል ወደ ስልጣን ከወጡ በኋላ ስልጣን መልቀቅ ከከበዳቸው 10 የአለም ሀገራት አምስቱ በአፍሪካ ይገኛሉ።
ከ1979 ጀምሮ የምዕራብ አፍሪካዊቷን ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ መምራት የጀመሩት ቲወዶር ኦቢያንግ ንጉይማ ለአራት አስርት መርተውም ስልጣን የሙጥኝ እንዳሉ ናቸው።
ሶቪየት ህብረት ከመፈራረሷ ከ10 አመት በፊት የመጀመሪያውን የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በሀይል ገልብጠው ስልጣን የያዙት ቲወዶር አቢያንግ ሀገራቸውን “የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ” የሚል ተቀጽላ አሰጥተዋል።
የአለማችን የእድሜ ባለጠጋው የሀገር መሪ ፖል ቢያም በካሜሮን የቲወዶርን መጥፎ ልማድ ተክለዋል።
የ91 አመቱ ፕሬዝዳንት ከ1982 ጀምሮ ሰባት ተከታታይ ምርጫዎችን አሸንፌያለው በማለት በስልጣን ላይ ናቸው።
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒም ከወንበሬ የሚነቀንቀኝ የለም በሚል ላለፉት 38 አመታት የምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር እየመሩ ነው።
ላለፉት 30 አመታት ኤርትራን በፕሬዝዳንት በመምራት ላይ የሚገኙት ኢሳያስ አፈወርቂም ለረጅም አመታት ስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ከ1999 ጀምሮ ሩሲያን በመምራት ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም በክሬምሊን እስከ 2030 የሚያቆያቸውን ድምጽ በቅርቡ በተካሄደ ምርጫ ማግኘታቸው ይታወሳል።
ለረጅም አመታት በስልጣን ላይ ያሉ 10 መሪዎችን ይመልከቱ፦