በጥናቱ መሰረት 63 በመቶ ምላሽ ሰጭዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እምነት አላቸው ተብሏል
የሩሲያ ዜጎች በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ያላቸው የመተማመን ደረጃ መጨመሩን በሀገሪቱ የተሰራ ጥናት አመለከተ።
የሩሲያን የሕዝብ አስተያየት ጥናት ማዕከል ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት የሩሲያ ሕዝብ በቭላድሚር ፑቲን ላይ ያለው እምነት እየጨመረ ነው።
በዚህም መሰረት ጥናት ከተደረገባቸው ሰዎች መካከል 81 ነጥብ 3 የሚሆኑት በፑቲን ላይ እምነት አላቸው።
የሩሲያ ዜጎች በፕሬዝዳንታቸው ላይ ያላቸው እምነት በቅርበ ጊዜ ውስጥ በ0.5 በመቶ መጨመሩም ነው የተገለጸው።
የጥናት ማዕከሉ ያካሄደውን መጠይቅና ዝርዝር ጥናት ይፋ ያደረገው ዛሬ ነው። የጥናት ማዕከሉ እንዳለው ብዙ ሰዎች ጥያቄ ሲቀርብላቸው የሰጡት ምላሽ አወንታዊ እንደሆነ ተገልጿል።
ለዚህ ጥናት ምላሽ የሰጡት ወጣቶች 1600 ሲሆኑ ጥናቱ የተሰራው በፈረንጆቹ ከነሐሴ 1 እስከ 7 ነው ተብሏል።
ከአውሮፓውያኑ ጥር 2020 ጀምሮ የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሚክሃይል ቭላድሚሮቪች ሚሹስቲን 63 ነጥብ 1 በመቶ በሚሆኑ ዜጎች እንደሚታመኑም ነው ጥናቱ ያመለከተው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ 2010 እስከ 2020 የፌዴራል ታክስ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
በሩሲያ የጥናት ማዕከል የተሰራው ጥናት በሀገሪቱ ምክር ቤት፤ በፓርቲዎችና በሌሎች ተቀማትና ግለሰቦች ላይም ጥናት አካሂዷል።