የሚሊየነሮች ፍልሰት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ከተነጠለች ጊዜ ጀምሮ ከ16 ሺህ በላይ ባለጸጎቿን አጥታለች
የግብር መጨመር፣የደህንነት ስጋት እና ኢንቨስትመንት ህጎች ባለጸጎችን እንዲለቁ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የሚሊየነሮች ፍልሰት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ባለጸጋዎች አመቺ መኖሪያ እና ሀገር ፈልገው በመኖር ይታወቃሉ፡፡ የተሸለ ደህንነት፣ አነስተኛ ግብር እና ለኢንቨስትመንት አመቺ በሚሉት ሀገርም ይኖራሉ፡፡
ይህን ተከትሎም በተጠናቀቀው የ2024 ዓመት ውስጥ ከ30 ሺህ በላይ ሚሊየነሮች ለዓመታት ይኖሩበት ከነበረበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ተሰደዋል ሲል ሄንሌይ ኤንድ ፓርትነርስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የጥናት ተቀወም ዘግቧል፡፡
ቻይና በ2024 ዓመት ብቻ 15 ሺህ ሚሊየነሮቿን ስታጣ ብሮታንያ ደግሞ 9 ሺህ 500 እንዲሁም ሕንድ 4 ሺህ 300 ሚሊየነሮቻቸውን አጥተዋል፡፡
ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ከተነጠለችበት ጊዜ ጀምሮ 16 ሺህ 500 ሚሊየነሮቿ ወደ ሌሎች ሀገራት ተሰደዋል፡፡
ደቡብ ኮሪያ፣ ብራዚል እና ሩሲያም በአንጻራዊነት ብዙ ባለጸጎቻቸውን ካጡ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣አሜሪካ እና ሲንጋፖር ደግሞ በርካታ ሚሊየነሮችን የተቀበሉ ሀገራት ናቸው፡፡