የገበያ መቀዛቀዝ እና የዋጋ ግሽበት ወነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተገልጿል
የዓለማችን ሚሊየነሮች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ።
የዓለማችን ባለጸጋዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ሲመጣ ቢቆይም በ2022 ዓመት ግን ቁጥራቸው እንደቀነሰ ተገልጿል።
ከፈረንጆቹ 2008 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለማችን ባለጸጋዎች ቁጥር መቀነሱን ሲኤንኤን ዘግቧል።
በተጠናቀቀው 2022 ዓመት ውስጥ ዓለማችን 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህል ባለጸጋዎች ከሚሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ እንደተቀነሱ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠመው የገበያ መቀዛቀዝ በተለይም የቦንድ እና አክስዮን ገበያ መቀነሱ ለባለጸጋዎቹ ሀብት መቀነስ ዋነኛው ምክንያቶች እንደሆኑ ተገልጿል።
1 ነጥብ 8 አሜሪካዊያን ባለጸጋዎች ከሚሊየነርነት ዝርዝር ውስጥ ተሰርዘዋል ተብሏል።
50 ሚሊዮን ዶባር እና ከዛ በላይ ያላቸው ባለጸጋዎች የናጠጡ ባለሀብቶች የሚባሉ ሲሆን 17 ሺህ 260 ያህል የናጠጡ ባለጸጋዎች ወደ ባለጸጋነት ዝርዝር ውስጥ እንደገቡም ተገልጿል።
ይሁንና አሜሪካ አሁንም 120 ሺህ የናጠጡ ባለጸጋዎች ወይም 50 ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ ሀብት ያላቸውን ዜጎች በመያዝ ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ናት።
ሁለተኛ የሆነችው ሀገር ደግሞ ቻይና ስትሆን 33 ሺህ የናጠጡ ባለጸጋዎች አሏት ተብሏል።
በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የዓለም ባለጸጋዎች ሀብት አሁን ካለበት 454 ትሪሊዮን ዶላር ወደ 629 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
የዓለም ሚሊየነሮች ዝርዝር ውስጥም በታዳጊ ሀገራት የሚገኙ ባለጸጋዎች የበለጠ ሀብት ያገኛሉም ተብላል።