ከዛሬ ጀምሮ አስከ እሁድ በሚቆየው የዓለማችን ውዱ ሰርግ ምን የተለየ ነገር አለው?
የህንዳዊው ቢሊየነር የሙኬሽ አምባኒ ልጅ አናንት አምባኒ የረዥም ጊዜ ፍቅረኛው ራዲካን በውድ ሰርግ ሊያገባ ነው
ለ3 ቀናትን በተካሄደ የቅድመ ጋብቻ ስነ ስርዓት ላይ እንደ ሪሃና፣ ማርክ ዙከርበርግና ቢል ጌትስ ያሉ ታዋቂ እንግዶች ታድመዋል
የዓለማችን ውድ ሰርግ ከዛሬ አርብ ጀምሮ እስከ ፊታች እሁድ ድረስ በህንዷ ሙንባይ ከተማ መካሄድ መጀመሩ ተነግሯል።
የህንዳዊው ቢሊየነር የሙኬሽ አምባኒ ልጅ አናንት አምባኒ የረዥም ጊዜ ፍቅረኛው ራዲካ ሜርቻንትን ድል ባለ የሰርግ ስነ ስርዓት ሊያገባ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተሰምቷል።
በፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ አናንት አምባኒ የረዥም ጊዜ ፍቅረኛው ራዲካ መርቻንትን ሊያገባ መሆኑን ይፋ ማደረጉን ተከትሎ በተዘጋጀ የቅድመ ጋብቻ ስነ ስርዓት ላይ ከ1 ሺህ 200 በላይ ታዋቂ እንግዶች መታደማቸው ይታወሳል።
በ3 ቀኑ የቅድመ ጋብቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙ ታወቂ ሰዎች እና ባለሃብቶች መካልም ሪሃና፣ ማርክ ዙከርበርግና ቢል ጌትስ ተጠቃሽ ናቸው።
ሪሃና በስነ ስርዓቱ ላይ የሙዚቃ ስራዎቿን ባታቀርብም በመታደሟ ባቻ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደተከፈላትም ነው በወቅቱ የወጣ መረጃ የሚያመለክተው።
በህንድ ሙናባይ በተካሄደው የቅድመ ጋብቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀረበው ጀስቲን ቢበር ደግሞ 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተከፍሎታል ነው የተባለው።
የቅድመ ጋቻ ስነ ስርዓታቸውን ያጠናቀቁት አናንት አምባኒ እና ራዲካ መርቻንት ይፋዊ የሰርግ ስነ ስርዓታቸው ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ለሶስት ቀናት በህንዷ ሙንባይ እንደሚከናወንም ተነግሯል።
የሰርግ ስን ስርዓቱ ከ16 ሺህ በላይ ሰዎችን በሚያስተናግደው ግዙፍ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማእከል እና ባለ 27 ፎቅ በሆነ የሙሽሮቹ ቤተሰቦች ቅንጡ ቤት ውስጥ ይከናወናል ተብሏል።
በዋናው የሰርግ ስነ ስርዓት ላይም የቀድሞ የአለም መሪዎችን፣ የቴክኖሎጂ ልሂቃንን እንዲሁም የሆሊውድ እና የቦሊውድ ኮከብ ተዋናዮችን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች እንደሚሳተፉበትም ተነግሯል።
የሰርግ ስነ ስርዓቱ ከሚካሄድበት ስፍራ አንዲ የሆነው የሙሽራው ቤተሰቦች መኖሪያ ቅንጡ ቪላ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን፤ መኖሪያ ቤቱ የግል ሲኒማና ቴአትር አዳራሽ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የአካል ብቃት ማዕከል እንዲሁም 160 መኪናዎችን የሚያቆም ስፍራ አለው።
የሙሽረው አባት ሙኬሽ አምባኒ በዓለም ላይ ካሉ ቢሊየነሮች ውስጥ ባላቸው የሀበት መጠን 9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ ከእሲያ ደግሞ 1ኛ ናቸው።
እንደ ፎርቢስ መረጃ ከሆነ የሙኬሽ አምባኒ አጠቃላይ ሀብት 116 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው።
በ2018 ሴት ልጃቸውን የዳሩት ቢሊየነሩ ሙኬሽ አምባኒ በህንድ እጅግ ውዱን ሰርግ በመደገስ ይታወቃሉ።
አሜሪካዊቷ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ቢዮንሴ የዘፈነችበት ሰርግ 100 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደተደረገበትም በወቅቱ ተነግሮ ነበር።