በዓለም በጣም ውድ የሆነው ዜሮ (ኔት ዜሮ) ምንድን ነው?
እስከ 2021 ድረስ 140 ሀገራት ይህንን ውድ ዜሮ ለማሳካት ቃል ገብተዋል
ይህን ውድ ዜሮ ለማሳካት እስክ ፈረንጆቹ 2050 ድረስ 115 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋል
ዓለማችንን ከካርበን ልቀት ነጻ ለማድረግ ውዱን ዜሮ ለማሳካት ሀገራት ቃል ገብተው መስራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
ዓለምን ከካርበን ነጻ ማድረግ (የካርበን ገለልተኝነት) ለማሳካት እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ 140 ሀገራት ቃል መግባታቸውም ይታወቃል።
በዚህም የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በፈረንጆቹ 2050 ቻይና ደግሞ በፈረንጆቹ በ2060 እቅዱን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
ከአረብ 3 ሀገራት ብቻ የካርበን ገለልተኝነት ላይ እየሰሩ ነው ነው የተባለ ሲሆን፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ባህሬን በ2050 እና በ2060 እቅዱን ለማሳካት ወጥነዋል።