ሶስቱ ታንኮች በበብቃታቸውና ጥንካሬያቸው በዓለም ላይ ምርጥ ተብለው የተለዩ ናቸው
ታንኮች ለዩክሬን ስላላቸው ጠቀሜታ ብዙ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት በዓለማችን ላይ አቅማቸው እና በተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ እና ወሳኝ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ጠንካራና አደገኛ ተባሉ ታንኮች ይፋ ተደርገዋል።
የአሜሪካው ኢንሳይደር ድህረ ገጽ በምድር ላይ ምርጥ ተብለው ሊታወቁ የሚገባቸው 3 ታንኮችን በማነጻጸር ይፋ አድርጓል።
እንደ ድረ ገጹ መረጃ የአሜሪካው “M1 አብረሃምስ”፣ የደቡብ ኮሪያ K2 ብላክ ፓንተር” እና የጀርመን ሊዮፓርድ “አውሬዎች” የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው የዓለማችን አደገኛ ታንኮች ናቸው።
የአሜሪካው “M1 አብረሃምስ” ታንክ
የአሜሪካው “M1 አብረሃምስ” የደቡብ ኮሪያ K2 ብላክ ፓንተር” እና የጀርመን ሊዮፓርድ ጋር ሲነጻፀረ ምርጡ ታንክ መሆኑ ተረጋግጧል።
አሜሪካ በኢራቅ ባካሄደችው ኦፕሬሽን ወቅት 1ከ1 ሺህ 800 በላይ “M1 አብረሃምስ” ታንኮችን አሰማርታ የነበረ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ጉዳት የደረሰባቸው 23 ብቻ እንደሆነ ኢንሳይደር አስታውቋል።
የደቡብ ኮሪያ “K2 ብላክ ፓንተር” ታንክ
“አስገራሚው አውሬ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የደቡብ ኮሪያ “K2 ብላክ ፓንተር” ታንክ ከመሬት አቀማመጥ ጋር ራሱን እያስተካከለ መጓዝ የሚችል አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ወደ ግራ አሊያም ወደ ቀኝ ማዘንበል የሚችል ነው።
በውጊያ ላይ የሚጠቀምባቸው ገዳይ መሳሪያዎች የተገጠሙለት ታንኩ፤ በተገጠመለት "KSTAM-II" ፕሮጄክታይል አማካኝነት የጠላትን ታንክ በፍጥነት በመለየት ወደ አመድነት የመለወጥ አቅም አለው ተብሏል።
እስከ 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኝ የጠላት ታንክን የሚመታ መድፍ የሚተኩስ መሆኑንም ነው ኢሳይደር ያስነበበው።
የጀርመን ሊዮፓርድ ታንክ
የጀርመኑ ሊዮፓርድ2 ታንክ በአውሮፓ ውስጥ ምርጡ ታንክ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፤ ከሰሞኑም ለዩክሬን ይሰጥ ከሚለው ጋር ስሙ ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።
1 ሺህ 500 የፈረስ ጉልበት ያለው ሞተር የተገጠመለት ታንኩ በሰዓት 67 ኪሎ ምትር ድረስየሚንፍ ሲሆን፤ እስከ 550 ኪሎ ሜትር ድረስ የማካለል አቅም አለው።
የጀርመን መከላከያ ሃይል ተቋም ካውስ ማፋይ ዋግማን ከፈረንጆቹ 1978 ጀምሮ ከ3 ሺህ 500 በላይ ሊዮፓርድ 2 ታንኮችን አምርቷል።
ከ60 ቶን በላይ የሚመዝነውና በናፍጣ የሚሰራው ታንክ እስከ 5 ኪሎሜትር ትክክለኛ ኢላማውን መምታት ይችላል። ፖላንድ፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ስዊድን እና ቱርክን ጨምሮ 20 ሀገራት ይህን ታንክ ይጠቀሙበታል።