በዓለም በቁመቱ ትልቁ እስር ቤት ሊገነባ ነው ተባለ
ከዓለም በቁመቱ አንደኛ የሆነው ይህ እስርቤት የሚገነባው በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ ነው
በአካባቢው ነዋሪዎች "ጄልስክራፐር" ወይም የእስረኞች ማማ በማለት የሚጠሩት ይህ ህንጻ 1040 ክፍሎች ይኖሩታል
በዓለም በቁመቱ ትልቁ እስር ቤት ሊገነባ ነው ተባለ።
ከዓለም በቁመቱ አንደኛ የሆነው ይህ እስርቤት የሚገነባው በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ ነው።
በኒው ዮርክ ከተማ የምትገኘው ቻይናታውን በርካታ የዳቦ አይነት ባላቸው ሱቆች፣ በጠባብ መንገዶቿ እና በጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብሯ ነበር በልዩ ሁኔታ የምትታወቀው።
ነገርግን በሶሆ እና ትሪቤካ መካከል ያለችው ይህች የማንሀተን መሀል ከተማ መንደር በሌላ ነገር ታዋቂ ሆናለች። መንደሯ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ በዓለም በቁመት ትልቁ እስር ቤት መገኛ ትሆናለች።
በአካባቢው ነዋሪዎች "ጄልስክራፐር" ወይም የእስረኞች ማማ ብለው የሚጠሩት ይህ 300 ጫማ ቁመት እና 1040 ክፍል ያለው ባለ40 ፎቅ ህንጻ የኢምፓየር ስቴት ህንጻን 1/3ኛ ይሆናል ተብሏል።
ይህ እስር ቤት አምስት ብሎኮች ላይ ጥላ የሚያጠላ እና በክረምት ወቅት አካባቢውን ወደ ጨለማ ሊቀይር የሚችል ነው።
በኃይት ስትሪት የሚኖሩት ሰዎች በጓሯቸው ባለው የማንሀተን ነባር እስርቤት ወይም ቶምብ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
ነገርግን ሰማይ ጠቀሱን እስር ቤት ለመስራት ቶምቡ ሲፈርስ አካባቢው በአቧራ መሞላቱ ነዋሪዎችን ቅር አሰኝቷል።
የአዲሱ ህንጻው ግንባታው ገና ያልተጀመረ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች በሂደት ለሚያጋጥማቸው ችግር ዝግጁ መሆናቸውን ለኒው ዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።
በ2019 የካውንስል ባለስልጣናት በማንሀተን ፣ በኩይንስ፣ በብሩክሊን እና ብሮክስ አዳዲስ እስርቤቶችን ለመገንባት 8.3 ቢሊዮን ዶላር መመደባቸውን አስታውቀው ነበር።
ቶምቡ በ2025 እንደሚፈርስ እና ሰማይ ጠቀስ በሆነ እስርቤት እንደሚተካ የፕሮደክቱ ኮንትራክተሮች ተናግረዋል።
በርካቶች ፕሮደክቱን ለአመታት ሲቃወሙ ከቆዩ በኋላ በ2020 ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከሰው ግንባታው በጊዜያዊነት እንዲቆም ማድረግ ችለው ነበር።
በቻይናታውን ከ57ሺ በላይ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 34,295 የሚሆኑት የእስያ ዝርያ ያላቸው መሆናቸውን በ2022 የወጣው ሪፖርት ያመለክታል።
ፕሮጀክቱን የሚቃወመው 'ዌልካም ቱ ቻይናታውን' የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርድት የቶምቡ ወይም የብሎኩ መፍረስ እና አዲስ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ የማቆም ተግባር በአካባቢው ላይ ከፍተኛ አደጋ ያስከትላል ብሏል።
ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ለማስቆም 12ሺ ሰዎች አቤቱታ አቅርበዋል።