ከፍተኛ የጾታ አለመመጣጠን ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ጦርነት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ወረርሽኞች እና የተዛባ የጾታ አመለካከት በሴት እና ወንድ መካከል ላለው አለመመጣጠን እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል
የባልካን ሀገራት ከፍተኛ የወንዶች እጥረት ከተከሰተባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
ከፍተኛ የጾታ አለመመጣጠን ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
እንደ መንግስታቱ ድርጅት የስነ ህዝብ ፖሊሲ ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን ካለው 8 ቢሊዮን ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ ወንዶች ከሴቶች በ40 ሚሊዮን ብልጫ አላቸው፡፡
ይሁንና በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ደግሞ የጾታ አለመመጣጠን ያለ ሲሆን በተለይም በአርመንያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ የሴቶች ድርሻ 55 በመቶ ሲሆን በዩክሬን ደግሞ 54 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
ቤላሩስ፣ ላቲቪያ፣ ዚምባብዌ እና ሩሲያም ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲነጻጸሩ አነስተኛ ቁጥር እንዳላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሴቶች ቁጥር ከወንዶች አንጻር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ሲሆን ሲሸልስ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ ከአፍሪካ ዝቅተኛ የሴቶች ህዝብ ብዛት ያለባቸው ሀገራት ተብለዋል፡፡