ብስክሌቱ ከፊትና በኳላ በመሆን በ2 ሰዎች የሚነዳ ነው
በስምንት ኔዘርላናዳዊያን እንጂነሮች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራው የዓለማችን ረጅሙ የሚነዳ ብስክሌት በርዝመቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት መሆን ችሏል።
55.16 ሜትር የሚረዝመው ብስክሌቱ የአራት ባለፎቅ ባሶች ጋ እኩል ርዝመት ያለው ሲሆን፤ የዓለማች ረጅሙ ብስክሌት የሚል ክብረወሰን መቀዳጀት መቻሉ ነው የተነገረው።
ብስክሌቱን ከሰሩት ውስጥ አንዱ የሆነው የ39 ዓመቱ ኢቫን ቻለክ፤ ረጅሙ ብስክሌት ለመስራት ማሰብ የጀመረው በልጅነቱ ስለ ዓለም ረጅም ብስክሌት የጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ላይ ካነበበ በኋላ መሆኑን ተናግሯል።
ሆኖም ግን ረጅሙን ብስክሌት የመስራት ፕሮጄክቱን በፈረንጆቹ 2018 ላይ የጀመረ ሲሆን፤ በመሃል በኮቪድ ምክንያት የተቋረጠውን የሁለት ዓመት ጊዜ ሳይጨምር ከሌሎች አንጅነር ጓደኞቹ ጋር በመሆን ሳይክሉን እውን ለማድረግ 4 ዓመት ነው የፈጀበት።
ኢቫን ቻለክ፤ “ብስክሌቱን የሰራነው የጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ለመመዝገብ ዓላማ ይዘን ነው፤ ይህንን ለማሳካትም የጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ህጎች ድቦችን በደንብ በማጥናት ነው የሰራነው” ብሏል።
በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ደንብ መሰረት 55.16 ሜትር የሚረዝመውን ብስክሌት መንዳት የሚፈቀደው በ2 ሰዎች ሲሆን፤ ይህም አንድ ከፊትለፊት መሪ ላይ ሲሆን፤ አንደኛው ደግሞ ከኋላ ሆኖ ፔዳል በመምታት ይነዳሉ።
በዚህም መሰረት ኔዘርላናዳዊያን እንጂነሮች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራው እና 55.16 ሜትር የሚረዝመው ብስክሌ ዓለማችን ረጅሙ ብስክሌት በመሆን በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ መስፈር ችሏል።