ኢኳቶሪያል ጊኒን ለ43 አመታት የመሩት ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን ሊያራዝሙ ይፈልጋሉ ተባለ
የ80 አመቱ ኦቢያንግ በ1979 አጎታቸውን ፍራንሲስኮ ማኪያስን ከስልጣን በማስገድ ወደ መሪነት የመጡ መሆናቸው ይታወቃል
ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ለረዥም ጊዜ በስልጣን በመቆየት በዓለማችን አቻ ያልተገኘላቸው መሪ ናቸው
ለ43 አመታት የኢኳቶሪያል ጊኒ የመሪነትን በትርን በመጨበጥ በዓለማችን አቻ ያልተገኘላቸው ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ስልጣናቸው ሊያራዝሙ እንደሚፈልጉ ተገለጸ፡፡
ለዚህም ፕሬዝዳንቱ በኢኳቶሪያል ጊኒ በዛሬው እሁድ ዕለት እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ ምርጫ በማሸነፍ ስልጣናቸው እንደሚያረዝሙ ይጠበቃል፡፡
ታዛቢዎች እንሚሉት ከሆነም ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ እንሚያሸነፉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
የ80 አመቱ ኦቢያንግ ቀደም በተደረጉ ምርጫዎች ሁሉ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉም ነው ታዛቢዎቹ በመከራከሪያነት የሚያቀርቡት፡፡
"በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ኦቢያንግ ሙሉ በሙሉ እንሚያሸነፉ ጥርጣሬ የለውም" ሲሉ የአፍሪካ ስጋት የስለላ ድርጅት ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ማጃ ቦቭኮን ቬሪስክ ማፕሌክሮፍት ማናገራቸውም ሮይተርስ ዘግቧል።
"የድንበር መዘጋት እና የተቃዋሚ ደጋፊዎች ወከባ እና እስራት የኦቢያንግ የ43 አመት የስልጣን ዘመን እንዲራዘም መንገድ እየከፈተ ነው" ሲሉም አክለዋል ተንታኟ፡፡
እንደ ማጃ ቦቭኮን ሁሉ በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚደረገው ምርጫ ፍትሃዊነት እንደሚጎድለው ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እና የመብት ቡድኖች ቅሬታቸው ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡
አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ነጸ እና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ በተለያዩ መግለጫዎች የጠየቁ ሲሆን በተቃዋሚዎች እና በሲቪል ማህበራት ላይ የሚደርሰውን ትንኮሳ እና ማስፈራሪያ የተመለከቱ ሪፖርቶች እንደሚያስቧቸው ገልጸዋል፡፡
መንግስት ሪፖርቶቹን ውድቅ በማድረግ ሀገራቱ በምርጫ ሒደቱ ውስጥ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙ አሳስቧል።
በአሁኑ ምርጫ ወደ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ሀገር ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ለመመረጥ ለምምረጥ የተመዘገቡ ሲሆን፤ መራጮች 100 የምክር ቤት አባላት፣ 55 ሴናተሮች እና የአካባቢ ከንቲባዎችን ለመምረጥ ድምጽ የሚሰጡ ይሆናል።
ፕሬዝዳንት ለመሆን በሚደረገው ሩጫ ቡኤናቬንቱራ ሞንሱይ አሱሙ ከኦቢያንግ ጋር ለ6ኛ ጊዜ በእንዲሁም አንድሬስ ኢሶኖ ኦንዶ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተፎካከሩ።
እንደፈረንጆቹ በ 1968 ኢኳቶሪያል ጊኒ ከስፔን ነጻ ከወጣች በኋላ ሁለት ፕሬዚዳንቶች ብቻ የመሯት ሲሆን፤ ሁለተኛው የሆኑት ኦቢያንግ አጎታቸውን ፍራንሲስኮ ማኪያስ ንጉዌማን በ1979 መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን በማባረር በትረስልጣን ጨብጠው አስካሁን መዝለቃቸው ሚታወቅ ነው፡፡